ኢትዮጵያ፣ አውሮፓ ኅብረት ወደ አገራቸው ሊባረሩ የማይችሉ ጥገኝነት ጠያቂዎችን ለመላክ ከመረጣቸው አገራት መካከል አንዷ መኾኗን ሂውማን ራይትስ ዎች ገለጠ።
ተቋሙ፣ ኅብረቱ ጥገኝነት ጠያቂዎችን ወደ ሦስተኛ አገራት ለመላክ አዲስ ስልቶችን እየቀየሠ ይገኛል በማለት ወቅሷል።
ጀርመን፣ ኦስትሪያ፣ ዴንማርክ፣ ግሪክ እና ኔዘርላንድስ ጥገኝነት ጠያቂዎችን ለመላክ ከመረጧቸው አገራት መካከል፣ ኢትዮጵያ፣ ኡጋንዳ፣ ሩዋንዳ፣ ቱኒዚያ፣ ግብጽ፣ ሊቢያ እና ሞሪቴኒያ እንደሚገኙበት ተቋሙ ጠቅሷል።
ተቋሙ፣ ተቀባይ አገራት የጥገኝነት ጠያቂዎቹን ሰብዓዊ መብት ያከብሩ፣ ወደ ትውልድ አገራቸው ይመልሷቸው ወይም ያስሯቸው እንደኾነ ግልጽ አይደለም ሲል ስጋቱን ገልጧል።
የኅብረቱ አገራት ይህንኑ እቅድ እንዲተውት ያሳሰበው ተቋሙ፣ ይህ ካልሆነ ግን እቅዱ ተግባራዊ ከመኾኑ በፊት ኅብረቱ ቢያንስ በተቀባይ አገራት የሰብዓዊ መብት አያያዝ ላይ ጥብቅ ግምገማ እንዲያደርግ እቅዱን የሚቃወሙት የፈረንሳይና ስፔን መሪዎች ግፊት እንዲያደርጉ ጠይቋል።
@Seledadotio

No comments yet.