የሆሳዕናው የውሻ ግድያ 2 ህጻናት ተማሪዎች በእብድ ውሻ በሽታ መሞታቸውን ተከቶሎ የተፈፀመ ነው‼️
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሆሳዕና ከተማ በራቢስ (የእብድ ውሻ) በሽታ ምክንያት ከአንድ ቤት የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎችን ጨምሮ የሰዎች ሕይወት ማለፉን ተከትሎ፣ በነዋሪዎችና በእድር አማካኝነት ሰፊ የውሻ ግድያ ዘመቻ መጀመሩ ትልቅ መነጋገሪያ ሆኗል። በከተማዋ አስተዳደር ግብርና ጽሕፈት ቤት መረጃ መሠረት በሆሳዕና ከተማ ውስጥ በአጠቃላይ ከ 10,500 በላይ ውሾች የሚገኙ ሲሆን፣ ከእነዚህ ውስጥ 7,500 የሚሆኑት ባለቤት ያላቸው ሲሆኑ 7,200 ያህሉ የተከተቡ ናቸው።
ይሁን እንጂ ቀሪዎቹ 3,000 የሚጠጉት ውሾች ባለቤት የሌላቸውና በየአደባባዩ የሚገኙ በመሆናቸው ለበሽታው መስፋፋትና ለሕዝብ ስጋት ዋነኛ ምክንያት መሆናቸው ተገልጿል።
የሰው ሕይወት መጥፋቱን ተከትሎ በተፈጠረ ድንጋጤ ነዋሪዎች ጤነኛ የሆኑና የተከተቡ የቤት ውሾችን ጭምር በገመድ በማነቅና በተለያዩ መሣሪያዎች በጭካኔ እየገደሉ መሆኑን የገለጹት የከተማው ግብርና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተመስገን ለፋሞ፣ ይህ ዓይነቱ ድርጊት የእንስሳትን ጤናና ደህንነት ለመጠበቅ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 1376/2017 የሚጻረርና በሕግ የሚያስጠይቅ በመሆኑ ድርጊቱን የማስቆም ሥራ እየተሠራ መሆኑንና ከጸጥታ አካላት ጋር በመሆን ጥፋተኞችን ለመለየት መረጃ እየተሰበሰበ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።
@Seledadotio

- Advertisement -

No comments yet.