ዩስራ ሆም ሁለተኛውን የአሽሊ ፈርኒቸር ቅርንጫፍ ከፈተ

- Advertisement -
Sidebar AD

በአሜሪካ ለ80 ዓመታት አለም አቀፍ ብራንድ ሆኖ የዘለቀው አሽሊ ፈርኒቸር ለዩስራ ሆም በሰጠው የብቸኛ ወኪልነትና አቅራቢነት ፍቃድ ኢትዮጵያ ውስጥ ሁለተኛ ቅርንጫፉን ከፍቷል።

ባለፈው ጥር ወር የመጀመሪያውን ቅርንጫፍ ዩስራ ሆም ብስራተ ገብርኤል አካባቢ መክፈቱ የሚታወቅ ሲሆን ዛሬ ደግሞ ሁለተኛ ቅርንጫፉን በጉርድ ሾላ ማሳያው አስመርቋል።

ከ155 በላይ ሃገራት ታዋቂ የሆነው አሽሊ ፈርኒቸር የኢትዮጵያን ገፅታ በመልካም ጎን በማሳየትና አለም አቀፍ ግንኙነቷን በማጠናከር ረገድ የራሱን ሚና እንደሚያበረክት ይታመናል።

የአሜሪካ አምባሳደር ለኢትዮጵያ ኤርቪን ማሲንጋ፣ የዩስራ ሆም መሥራችና ዋና ስራ አስፈፃሚ ዩስራ ኑርሁሴን ረጃ፣ እንዲሁም የአሽሊ ፈርኒቸር የሥራ መሪዎች በተገኙበት ቅርንጫፉ በይፋ የተመረቀ ሲሆን ታላላቅ የንግድ ሰዎች፣ ዲፕሎማቶች እና የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ታድመው ነበር።

እንደሚታወቀው ኢትዮጵያ እያስመዘገበችው ያለው የቱሪዝም ዘርፍ ዕድገት እና በመላ ሀገሪቱ እየተስፋፋ የመጣው የዘመናዊ ሆቴሎች ግንባታ፣ የዓለም አቀፍ ግዙፍ ኩባንያዎችን ትኩረት እየሳበ ይገኛል።

በዓለም የፈርኒቸር ኢንዱስትሪ ቀዳሚ የሆነው የአሜሪካው አሽሊ ፈርኒቸር ወደ ኢትዮጵያ ገበያ በይፋ መግባቱ፣ የሀገሪቱን የግንባታና የእንግዳ ተቀባይነት (Hospitality) ዘርፍ ተስፋ ይበልጥ የሚያጠናክር መሆኑም ተገልጿል።

ኢትዮጵያ ያላትን የተፈጥሮ፣ የታሪክ እና የባህል ፀጋዎች በመጠቀም አዳጊ የቱሪዝም ተስፋ ካላቸው የአፍሪካ ሀገራት መካከል ግንባር ቀደሟ እየሆነች ትገኛለች ያሉት የዩስራ ሆም መሥራች ወይዘሮ ዩስራ ኑር ሁሴን ሲሆኑ ድርጅታቸው የመጀመሪያውን የአሽሊ ፈርኒቸር ቅርንጫፍ በከፈተ በ6ወሩ ሁለተኛውን በይፋ በማስመረቁ ታላቅ ኩራት ይሰማዋል ብለዋል።

በአሽሊ ፈርኒቸር የአፍሪካ እና የእንግሊዝ ምክትል ፕሬዚዳንት ማርክ ማራስ በምረቃ መርሀ ግብሩ ዕለት በሰጡት መግለጫ ዩስራ ሆም ከአሽሊ ፈርኒቸር የሚጠበቀውን መስፈርት አሟልቶ በመገኘቱ የወኪልነት እና የአቅራቢነት ማረጋገጫ መስጠቱን ተናግረዋል። አሽሊ ፈርኒቸር በፍሬንቻይዝ ለዩስራ ሆም ምርቶቹን በማቅረቡ ኩራት ይሰማዋል ሲሉም ሚስተር ማርክ ተናግረዋል።

የአፍሪካ መዲና የሆነችው አዲስ አበባ ዕድገቷ የሚታይ እና እኛ ልንፈጥር ላሰብነው ገበያ የምትመች ናት ሲሉም ለከተማዋ ያላቸውን አድናቆት ገልፀዋል።

ወይዘሮ ዩስራ ኑርሁሴን የዩስራ ሆም መስራች አሽሊ ፈርኒቸርን ወደ አገር ቤት ለማስገባት ሁለት ዓመት እንደወሰደባቸው ተናግራ ወደፊት ደግሞ ተጨማሪ ቅርንጫፍ ይከፈታል ብለዋል።

አጥኚዎች እንደሚናገሩት የቱሪዝም ፍሰት እና የዓለም አቀፍ ጉባኤዎችን መስተንግዶ ተከትሎ፣ በአዲስ አበባ እና በተለያዩ የቱሪስት መዳረሻዎች የኮከብ ደረጃቸውን የጠበቁ ዘመናዊ ሆቴሎች እና የመዝናኛ ስፍራዎች ግንባታ በከፍተኛ ፍጥነት እየተበራከቱ መጥተዋል።

ይህ እያደገ የመጣው የሆቴሎች እና የሕንፃዎች ግንባታ ደግሞ ከፍተኛ ጥራት እና ዘመናዊ ዲዛይን ያላቸው የቤትና የቢሮ ዕቃዎች ፍላጎትን በከፍተኛ ደረጃ ጨምሮታል በሚለው ሁሉም አጥኚዎች የሚስማሙበት ሐቅ ነው።

የአሽሊ ፈርኒቸር ወደ ኢትዮጵያ መግባት ከሀገሪቱ የቱሪዝም እና የግንባታ ዘርፍ ጋር ያለውን ግንኙነት ያጠናክረዋል ሲሉ የዩስራ ሆም የሥራ መሪዎች ይናገራሉ።

ለአብነትም አዳዲስ ለሚገነቡ እና ነባር ለሆኑ ሆቴሎች፣ ሬስቶራንቶች እና ሎጆች ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ፣ ዘመናዊና ምቹ የፈርኒቸር ምርቶችን በሀገር ውስጥ በቀላሉ ለማቅረብ ያስችላል።
በተጨማሪም ቀደም ሲል ሆቴሎች እና አልሚዎች ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን ዕቃዎች ለማግኘት ወደ ውጭ ሀገር በመጓዝ ያወጡት የነበረውን ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ እና የትራንስፖርት ወጪ በከፍተኛ ደረጃ ይቀንሳል።

የ80 ዓመታት ልምድ ያለው የአሽሊ ፈርኒቸር የንድፍ እና የጥራት ደረጃዎች ወደ ሀገር ውስጥ መግባታቸው፣ ለሀገር ውስጥ የፈርኒቸር ባለሙያዎች የዕውቀት ሽግግር እንደሚፈጥርም በምረቃ መርሀ ግብሩ ላይ ተነግሯል።

ደንበኞች እና የሆቴል ባለሀብቶች እነዚህን ለአጠቃቀም ምቹ እና ዘመናዊ የሆኑ የአሽሊ ፈርኒቸር ምርቶችን በአዲስ አበባ ከተማ በቦሌ አትላስ በሚገኘው ሴንቸሪ ኤግዚኪውቲቭ ታወር እንዲሁም በብሥራተ ገብርኤል ኦልማርት ሱፐርማርኬት ህንፃ ላይ በሚገኙት የዩስራ ሆም ማሳያ ማዕከላ፣ አሁን ደግሞ ጉርድ ሾላ ከሚገኘው ማሳያ ማግኘት እንደሚችሉ ተጠቁሟል።

በአጠቃላይ የአሽሊ ፈርኒቸር እና የኢትዮጵያ ግንኙነት መጀመር፣ የሀገሪቱን የንግድ ኢንቨስትመንት ከማሳደጉም በላይ የቱሪዝም ዘርፉ የሚፈልገውን ዘመናዊና ማራኪ ገፅታ ለመገንባት ትልቅ አቅም ይፈጥራል ተብሎ ይጠበቃል።

የመርሀ ግብሩ የሚድያ ይዘት ዝግጅት በተወዳጅ ሚድያና ኮምዩኒኬሽን የሚሰናዳ ሲሆን ተወዳጅም ከዩስራ ሆም ጋር ህጋዊ የሥራ ውል በመፈራረም የአሽሊ ፈርኒቸርን ወደ አገር ውስጥ መግባት አስመልክቶ የመገናኛ ብዙሀንን የማስተባበር ሥራውን እንደሚያከናውን ለማወቅ ተችሏል።






Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1