#Ethiopia | ሉዊስ ሱዋሬዝ ወጣቱን የባርሴሎና ድንቅ ተጫዋች ላሚን ያማልን ከእግር ኳስ ሊቁ ሊዮኔል ሜሲ ጋር ማወዳደር ፍትሐዊ እንዳልሆነ ገለጸ።
ሱዋሬዝ በሰጠው አስተያየት ሁለቱም ተጫዋቾች አስማታዊ የግራ እግርና እጅግ አስደናቂ የሆነ ፈጣን አዕምሮ ያላቸው ቢሆንም ሙሉ በሙሉ የተለያዩ ተጫዋቾች ናቸው ብሏል።
በመሆኑም በሁለቱ መካከል የሚደረገው ንፅፅር አሁን ላይ መቆም እንዳለበት የጠቆመው የቀድሞው የባርሳ ኮከብ ወደፊት ግን ያማል የራሱን ታሪክ እየሠራ ቢያንስ የሜሲን ታላቅ ደረጃ መድረስ እንዲችል ያለውን ተስፋና መልካም ምኞት ገልጿል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
Source: GetuTemesgen









No comments yet.