#Ethiopia | በአዲስ አበባ ከተማ የደንብ ጥሰት 81 ነጥብ 2 በመቶ መቀነሱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን አስታወቀ።
የ2018 በጀት ዓመት የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርትን ያቀረቡት የባለስልጣኑ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ እንደገለጹት፤ በ2018 በጀት ዓመት በተቋም ግንባታ፣ በደንብ ማስከበርና በቴክኖሎጂ አጠቃቀም በርካታ ስራዎችን አከናውኗል።
የደንብ ጥሰት በሚፈጽሙ አካላት ላይ እርምጃ በመወሰዱና ህብረተሰቡ የደንብ ጥሰት ጠል እንዲሆን በተሰጠው የግንዛቤ ማስጨበጫ መሰረት የከተማዋ የደንብ ጥሰት 81 ነጥብ 2 በመቶ መቀነሱን ተናግረዋል።
ህብረተሰቡን በማሳተፍ የደንብ ጥሰትን ለመከላከል ቀደም ሲል በቀን 12 ሰዓት ብቻ አገልግሎት ሲሰጥ የነበረው 9995 ነጻ የስልክ መስመር አሁን ላይ ዲጅታል ተደርጎ 24 ሰዓት አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን አመላክተዋል፡፡
ነጻ የስልክ መስመሩ በአምስት ቋንቋዎች በቀን ከ200 እስከ 500 ጥቆማዎችን እየተቀበለ መሆኑን እና በርካታ የደንብ ጥሰቶችን ለመከላከል ማስቻሉን ዋና ዠሥራ አስኪያጁ ገልጸዋል ያለው ፕረስ ነው።
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
Source: GetuTemesgen









No comments yet.