የተወደደች ቀን የተመረጠች ዕለት
ቅድስት ቤተክርስቲያንን ለመዘከር ሳምንቱን ከቅዱስ ፓትርያርኩ ጀምሮ አበው ሊቃነ ጳጳሳትን እንዲሁም ለቅድስት ቤተክርስቲያን ራሳቸውን ሰጥተው ዋጋ በመክፈል ያገለገሉ እና እያገለገሉ ያሉ ማኅበራትን፣ ተቋማትንና ግለሰቦችን እንኳን አደረሳችሁ በማለትና በምሽት መርሐግብራት ቅድስት ቤተክርስቲያንን ሲዘክር የቆየው ማኅበራችን ሐመረ ብርሃን ማጠቃለያ መርሐግብሩን ዛሬ ሰኔ 20 የቅድስት ቤተክርስቲያንን በዓል መንፈሳዊ ድባብ በሰፈነበት ታላቅ ድምቀት አከበረ።
የሁላችን እናት፤ የቤተክርስቲያናችን ዝክር ውበቷ የሆኑ አበው መነኮሳትና የጉባኤ ቤት መምህራን፤ የሐመረ ብርሃን የአገልግሎት አጋር ማኅበራትና የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ሕፃናትና ወላጆቻቸው በተገኙበት ቦሌ መድኀኔዓለም ቤ/ክ አዳራሽ ሰኔ 20/2018ዓ.ም ተዘከረ።
በመርሐግብሩ ፍጻሜ ምዕመናን ቤታቸው ሄደው ቅድስት ቤተክርስቲያንን ከቤተሰቦቻቸው፣ ከወዳጆቻቸው እና ከጎረቤቶቻቸው ጋር የሚዘክሩበት የዝክር ጥቅል የተበረከተላቸው ሲሆን ይህም ዕለቱ ሁሉም ክርስቲያን እናት ቅድስት ቤተክርስቲያንን ዘክሮ ያሳልፍ ዘንድ አደራ ጭምርም ለማስተላለፍ የተደረገ ነው።
እናታችን ቅድስት ቤተክርስቲያን ሆይ እንወድሻለን፤ ለምኝልን!
ክርስቶስ አምላካችን ሆይ ሙሽራህ የሆነች እናታችን ቅድስት ቤተክርስቲያንን ጠብቅልን!



Source: Yeneta Tube









No comments yet.