ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በአራት የፖለቲካ ፓርቲዎች የተመሰረተው ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት ሀገርን አፅንቶ ለማስቀጠል እውነተኛ የፖለቲካ ድርድር እንዲካሄድ ጠይቋል።
የፓርቲዎቹ ስብስብ መንግሥት ወደ እውነተኛ ድርድር እስከሚመጣ ድረስ ሰላማዊ የፖለቲካ ትግሉን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ገልጿል።
በሀገር ብሔራዊ ጥቅም ጉዳይ የማይደራደር አቋም እንዳለውም ይፋ አድርጓል።
የትብብሩ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ጌትነት ወርቁ ከአሐዱ መድረክ ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ መንግሥት ምርጫ አሸንፌያለሁ በሚል ባለፉት ዓመታት ይከተለው በነበረው መንገድ የሚቀጥል ከሆነ ሀገርን አደጋ ላይ ይጥላል ብለው እንደማያምኑ ገልጸዋል።
ትብብሩ ምርጫው ይደገም የሚል አቋም እንደሌለውም ኃላፊው አብራርተዋል።
“ለተፈጠሩ ችግሮች እልባት ለመስጠት የድርድር ሂደቱን መጀመር ለነገ የማይባል ተግባር ነው” ያሉት አቶ ጌትነት የዲሞክራሲ ሥርዓት ባልዳበረባት ኢትዮጵያ የተፈጠሩ ችግሮች በአንድ ጊዜ ሙሉ በሙሉ ይፈታሉ የሚል እምነት እንደሌላቸው ጠቁመዋል።
ትብብሩ ያስቀመጣቸው ቅድመ ሁኔታዎች ምላሽ እስከሚያገኙ ድረስ ከሥርዓቱ ጋር የሚያደርገውን ሰላማዊ የፖለቲካ ትግል አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አቋሙን በድጋሚ አስታውቋል።
#አሐዱ
Source: Yeneta Tube








No comments yet.