#Ethiopia – የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ2026 የእስያ ጭነት፣ ሎጂስቲክስ እና አቅርቦት ሰንሰለት ሽልማት ሥነ ሥርዓት ላይ “የአፍሪካ ምርጥ የአየር ጭነት አጓጓዥ አየር መንገድ” በመባል ተሸላሚ ሆኗል።
ሽልማቱ ለኢትዮጵያ ካርጎ እና ሎጂስቲክስ አገልግሎት በዓለም አቀፍ የጭነት ማጓጓዣ ዘርፍ ያስመዘገበውን ውጤታማ አፈጻጸም፣ የአገልግሎት ጥራት እና የፈጠራ ሥራዎች እውቅና በመስጠት የተበረከተ ነው።
የአየር መንገዱ መረጃ እንደሚያመለክተው፣ ተቋሙ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተገነቡ የካርጎ መሠረተ ልማቶች፣ ስልታዊ አጋርነቶች እና ዘመናዊ የሎጂስቲክስ ሥርዓቶችን በመጠቀም የዓለም አቀፍ የንግድና የአቅርቦት ሰንሰለት ትስስርን ለማጠናከር እየሠራ ይገኛል።
በተጨማሪም ሽልማቱ የተሰጠው በዘርፉ ባለድርሻ አካላትና በደንበኞች በተሰጠ ከፍተኛ ድምፅ መሠረት መሆኑን አየር መንገዱ ገልጿል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለዚህ ስኬት አስተዋጽኦ ላበረከቱ ደንበኞቹ፣ የንግድ አጋሮቹ እና ሰራተኞቹ ከልብ ምስጋናውን አቅርቧል።
Source: GetuTemesgen









No comments yet.