የፌደራል ጠበቆች ማህበር በአዋጅ የመቋቋም አስፈላጊነት

- Advertisement -
Sidebar AD

በኢትዮጵያ ህግ ማእቀፍ

ጠበቃና የህግ አማካሪ ፋንታሁን ደለለው 0929101037
መግቢያ
#Ethiopia | የፍትህ ስረአትን ለማሳደግ የግ ባለሙያዎች ሚና ዋና ቁልፍ መሠረታዊ ድርሻ ያላቸው ስለመሆኑ የሚያጠያይቅ አይደለም። ይሁን እንጂ እነዚህ የህግ ባለሙያዎች ለፍትህ ስረአቱ አጋዥ ሀይል እንዲሆኑ አቃፊ የሆነ የፍትህ ስረአት መዋቅር ሊኖር ያስፈልጋል።

ይህ ሲኖር የህግ ባለሙያዎች በእውቀት፣ልምድ፣ስነምግባር እና ህግ በሚጠይቀው ድርሻ በመሳተፍ የበኩላቸውን ድርሻ ለሀገራቸው ፍትህ ስረአት አስተዋጽኦ የበኩላቸውን ጉልህ ድርሻ ሊወጡ የሚችሉበትን እድል በፍትህ ስረአት አወቃቀር ሊበጅላቸው ያስፈልጋል።

ለዚህ ደግሞ ህግ አውጭው አካል የአንበሳውን ድርሻ ስለመውሰዱ የማይካድ ሀቅ ነው። ጠበቆች በሀገር ደረጃ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ሲሆን የህግ ባለሙያዎች አጠቃላይ ሲቆጠሩ ቁጥራቸው ብዙ እና የኢትዮጵያ ህግ ገላጭ፣አስኪያጅ ስለመሆናቸው አጠራጣሪ አይደለም ።

ይህ ከሆነ ታዲያ “በአዋጅ ደረጃ እወቅና ኖርዋቸው ለኢትዮጵያ ፍትህ ስረአት እድገት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ ለምን ህጋዊ እውቅና አንሰጣቸውም” የሚለው የዚህ ጹሁፍ መነሻችን እና የህግ ህግዛቤ ገለጻችን ነው ፤ በጽሞና ይገንዘቡን።

1. የኢትዮጵያ ጠበቆች ማህበር በአዋጅ መቋቋም አስፈላጊነት

በኢትዮጵያ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ጠበቆች የሚገኙ ሲሆን እነዚህ ጠበቆች በኢትዮጵያ ፍትህ ስረአት ውስጥ እንደ ዝንባሌያቸው ፣እውቀታቸው፣ልምዳቸው፣ስነምግባራቸው፣የትምህርት ደረጃቸው፣እንደ ልዩ እውቀታቸው እንዲያገለግሉ አስፈላጊውን ሁሉ በማመቻቸት አገልግሎታቸውን በብቃት እንዲመሩ ያስችል ዘንድ በነጻነት በማስተዳደር ሙያዊ ነጻነታቸውን ከፍትሀዊ ተጠያቂነት ጋር አመዛዝኖ በህግ መሠረት በማስኬድ የማህበረሰቡን የፍትህ አገልግሎት ጥያቄ በጠበቆች ሙያዊ ብቃት እና ክህሎት እንዲመለስ አስፈላጊ በመሆኑ የኢትዮጵያ ጠበቆች ማህበር በአዋጅ መቋቋሙ አስፈላጊ ነው ብዬ አምናለው።

2. አሁን ያለበት ህጋዊ እውቅና እና የአስተዳደር ተግዳሮት

አሁን ላይ የጠበቆች ማህበር በራሱ የሚተዳደር የፍትህ ተቋም ወይም ሚኒስተር መስሪያ ቤት ሳይሆን በፌደራል በጥብቅና ምዝገባና ፍቃድ አሰጣጥ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1233/2013 የሚተዳደር ሲሆን ይህ የፌደራል ጠበቆች ማህበር ስልጣን፣ተግባር፣ሙያዊ ነጻነት፣ የማህበሩን አስተዳደር ፣ ተጠያቂነት፣ የጥብቅና ፍቃድ አሰጣጥ የመሳሰሉትን ለፌደራል ጠበቆች ማህበር በህግ እውቅና ያለሰጠ የፌደራል ጠበቆች በሚፈለገው ልክ እንዲሰሩ ስልጣን የማይሰጥ የጠበቆችን ማህበር ለራሱ በህግ ሊሰጠው የሚገባን የህግ ስልጣን ለቁጥጥር እና ማስተዳደር ሲባል ለሌላ አካል የተሰጠ መሆኑን ያሳያል።

3. የኢትዮጵያ/ፌደራል/ ጠበቆች ማህበር በአዋጅ ቢቋቋም ኃላፊነቱን በአግባቡ ስለመወጣቱ ምን አስተማማኝ ነጥብ አለ? ተጠሪነቱስ ለማን ነው?

የኢትዮጵያ/ፌደራል/ ጠበቆች ማህበር በአዋጅ ቢቋቋም ኃላፊነቱን በአግባቡ ስለመወጣቱ ዋስትናው የኢፊድሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሚያወጣው አዋጅ ላይ በሚሰጠው መብት እና ግዴታ፣ስልጣን፣ተግባር፣ኃላፊነት መሠረት ይሆናል። ይህን በህግ የተቀመጠውን ኃላፊነት ስለመወጣቱ በተመለከተ ተጠሪነቱ ለራሱ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በመሆኑ ምክር ቤቱ በመከታተል የሚያርመውና የሚደግፈው ይሆናል።

4. ማጠቃለያ እና የህግ ምክረ ሀሳብ

ለኢትዮጵያ ፍትህ ስረአት እድገት የህግ ባለሙያዎች ድርሻ የአንበሳውን ድርሻ የሚወስድ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ በዋነኝነት በኢትዮጵያ በርከት ያሉ ቁጥር ያላቸው ጠበቆች ናቸው።

ጠበቆች በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ሲሆን ምንም እንኳን የጠበቆች ማህበር ተብለው የመደራጀት ባህሪ ቢኖራቸውም ከመተዳደሪያ ደንብ በዘለለ በራሳቸው አዋጅ ሊመሩ የሚያስችል ህግ የላቸውም።

ይልቁንም የፌደራል ጠበቆች ጥብቅና ፍቃድ አሰጣጥ እና ምዝገባ አስተዳደር አዋጅ ራሱን በቻለ ከጠበቆች ማህበር ውጭ በሆነ አመራር የሚተዳደር ሲሆን በሌላ አነጋገር የጠበቆች ማህበር
ለዚህ አስተዳደር ጥገኛ ነው ማለት ይቻላል።

ስለሆነም ጠበቆች ራሳቸውን በራሳቸው ነጻነትን እና ተጠያቂነትን ሚዛን በጠበቀ እንደ ሙያቸው ብቃት ረድፍ ሀገራቸውን እና ዜጎቻቹውን በአግባቡ እንዲያስተዳድሩ የጠበቆች ማህበር በአዋጅ ደረጃ ሊቋቋም ያስፈልጋል ።

ማጣቀሻ/reference/
1. የኢፌድሪ ህገመንግስት
2. የፌደራል ጠበቆች ፍቃድ ምዝገባና አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1233/2013

Fantahun Delelew 0929101037,0983337690
https://t.me/Fantahunlawyer
tiktok.com/@fantahun214
https://www.facebook.com/share/1EQM4ub9ED/


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1