የመንግሥት ኃላፊዎችን አምስት ዓመት የሚያስረው አዋጅ ፀደቀ።
#Ethiopia | መረጃን የደበቀ ማንኛውም የመንግሥት ኃላፊ አምስት ዓመት የሚያሳስረው አዋጅ በምክር ቤቱ ጸድቋል።
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የነጻ መረጃ ረቂቅ አዋጅን አጽድቋል።
የዚህ አዋጅ አላማ ሙስናን፣ ሕገ-ወጥ አሠራርን ወይም የሥራ ብቃት ማነስን ለመሸሸግ ሲሉ መረጃና ሰነድ የሚደብቁ ወይም እንዲጠፉ የሚያደርጉ የመንግሥት ኃላፊዎችን ተጠያቂ ማድረግ ነው።
ጥፋቱ በፍርድ ቤት የተረጋገጠበት የማንኛውም የመንግሥት ወይም የግል ድርጅት የበላይ ኃላፊ፣ የመረጃ ኃላፊ ወይም ትዕዛዝ ሰጪ አካል እስከ 5 ዓመት በሚደርስ እስራት ይቀጣል ይላል።
#የሕዝብተወካዮችምክርቤት
#የነጻመረጃረቂቅአዋጅ
#ጊጡተመስገንሚዲያኮሚኒኬሽን
#Getutemesgenmediacommunication
በአውሮፕላን አደጋው እስካሁኗ ደቂቃ ድረስ 11ሰዎች ሞተዋል።
#Ethiopia | በፈረንሳይ በደረሰ የአውሮፕላን መከስከስ አደጋ የ11 ሰዎች ሕይወት አለፈ።
በምስራቅ ፈረንሳይ ቶምብላይን ከተማ አቅራቢያ በደረሰ የአነስተኛ አውሮፕላን መከስከስ አደጋ አብራሪውን ጨምሮ የ11 ሰዎች ሕይወት አልፏል፡፡
ለአንድ ፓራሹት ማሰልጠኛ ት/ቤት አገልግሎት ሲሰጥ የነበረው ሲቭል አውሮፕላን ከናንሲ ኢሴይ አውሮፕላን ማረፊያ ተነስቶ ብዙም ሳይቆይ መከስከሱ ተመላክቷል፡፡
በተፈጠረው አደጋም አብራሪውን ጨምሮ በአውሮፕላኑ ውስጥ የነበሩ የ11ዱም ሰዎች ሕይወት ማለፉን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
ከሟቾች መካከል አምስቱ የትምህር ቤቱ ተማሪዎች ሲሆኑ አምስቱ ደግሞ መምህራን እንደነበሩ ተጠቁሟል፡፡
የፈረንሳይ ትራንስፖርት ሚኒስቴር በተከሰተው አሰቃቂ አደጋ የተሰማውን ሐዘን ገልጾ የአደጋውን መንስኤ ለማጣራት እየተሰራ መሆኑን አስታውቋል፡፡
#ፈረንሳይቶምብላይንከተማ
#ፈረንሳይየአውሮፕላንአደጋ
#ጊጡተመስገንሚዲያኮሚኬሽን
#Getutemesgenmediacommunication
Source: GetuTemesgen








No comments yet.