#Ethiopia | አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21፣ 2018 ዓ.ም. – የኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 2,882 ተማሪዎች በዛሬው ዕለት በደማቅ ሥነ ሥርዓት አስመርቋል።
ዩኒቨርሲቲው በመጀመሪያ፣ በሁለተኛና በሦስተኛ ዲግሪ፣ እንዲሁም በዲፕሎማና በሌሎች የሥልጠና መርሃ ግብሮች የተማሩ ተመራቂዎችን ለኅብረተሰቡ አበርክቷል።
በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ተሾመ ነቃጥበብ ለተመራቂዎቹ እንኳን ደስ አላችሁ በማለት የእንኳን ደስ ያለችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
ፕሬዚዳንቱ ዩኒቨርሲቲው የትምህርት፣ የእውቀትና የቴክኖሎጂ ሽግግር ማዕከልነቱን ለማጠናከር ዘመናዊ ስትራቴጂዎችን በመተግበር ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
በተጨማሪም ከቀድሞው በተሻለ ጥራትና ብቃት ያላቸው “አርአያ መምህራን” ለማፍራት የተቀናጀ የሥልጠና ስርዓት ተግባራዊ እየሆነ መሆኑን ጠቁመዋል።
እንዲሁም የትምህርት ፕሮግራሞቹን ከሀገሪቱ ወቅታዊ የትምህርት ፍላጎትና የሥራ ገበያ ፍላጎት ጋር በማጣጣም፣ ለተማሪዎችም ሆነ ለሀገር እድገት የሚጠቅሙ ማሻሻያዎችን በቀጣይነት እየተገበረ መሆኑን አስረድተዋል።


Source: GetuTemesgen








No comments yet.