ሴቶች ከወንዶች በላይ ረጅም ዕድሜ የሚኖሩበት ምክንያት ምንድን ነው?

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ሴቶች ከወንዶች አንጻር በአማካይ ከአምስት ዓመት የበለጠ የመኖር ዕድላቸው ሰፊ ነው።

የሴቶች ዕድሜ የአምስት ዓመት ብልጫ ያሳያል የተባለው ዓለም አቀፍ አማካዩ ተወስዶ እንደሆነ አጥኚዎች ይናገራሉ።

በእርግጥ ሴቶች ከወንዶች በበለጠ ለምን ለረዥም ዓመት እንደሚኖሩ ሳይንቲስቶች በትክክል አላወቁም።

ሌሎች ፍጥረታትን እንደ ማነጻጸሪያ ብንወስድ ወንድ ወፎች ከሴቶች በበለጠ ይኖራሉ።

በዩናይትድ ኪንግደም የሥነ ሕዝብ እና ዕድሜ ጥናት ተቋም ዳይሬክተር ፕሮፌሰር ሳራ ሀርፐር “በሁሉም አገራት ሴቶች ከወንዶች የበለጠ ይኖራሉ” ይላሉ።

ቁጥሩ ከአገር አገር ቢለያይም ጠቅለል ባለ ሁኔታ ሴቶች ከወንዶች ዘለግ ላለ ጊዜ ይኖራሉ።

በሩሲያ፣ ዩክሬን እና ቬትናም ሴቶች ከወንዶች በበለጠ ለ10 ዓመት ወይም ከዚያ በላይ ይኖራሉ።

በናይጄሪያ ደግሞ ያለው ልዩነት ጠባብ እንደሆነ ‘አወር ወርልድ ኢን ዳታ’ ያወጣው አሃዝ ያሳያል።

ሳይንቲስቶች እንደሚሉት ይህ ልዩነት የተፈጠረው ግላዊ ባህሪን ጨምሮ በማኅበራዊ ልዩነት ነው።

ፕሮፌሰር ሳራ በሩሲያ ወንዶች ዘንድ መጠጥ እና ሲጋራ በጣም መዘውተራቸው ልዩነት አምጥቷል።

በሌሎችም አገራት ወንዶች “ሕይወትን የሚያሳጥር” ባህሪ እንዳላቸው ይናገራሉ።

“አመጋገባቸውም ጤናማ አይደለም” ይላሉ ፕሮፌሰር ሳራ።

ወንዶች አዘውትረው ወደ ሕክምና አለመሄዳቸውን ባለሙያዋ ይጠቅሳሉ።

“ባለትዳር ወንዶችን አጋሮቻቸው ሆስፒታል ስለሚወስዷቸው የተሻለ ሕይወት አላቸው” ይላሉ።

በብዙ ማኅበረሰቦች ውስጥ ወንዶች “አደገኛ” የሚባል ሥራ እንደሚያከናውኑ እና ወንድነት “ራስን ለአደጋ ከማጋለጥ” ጋር እንደሚተሳሰር ይናገራሉ።

“ወንዶች በከፍተኛ መጠን በመኪና አደጋ፣ በግጭት፣ በግድያ፣ ራስን በማጥፋት ሕይወታቸውን ያጣሉ” ይላሉ።

በዩናይትድ ኪንግደም በአውሮፓውያኑ በ1960ዎቹ እና በ1970ዎቹ የፀረ ሲጋራ ንቅናቄ መደረጉ የሚሞቱ ወንዶችን ቁጥር ቀንሶ ነበር።

በወቅቱ በወንዶች እና በሴቶች መካከል ያለው በሕይወት የመኖር ልዩነት ጠብቦ እንደነበር ፕሮፌሰር ሳራ ያስረዳሉ።

የሰዎች አኗኗር ሊለወጥም በፆታዎች መካከል ያለው ልዩነት ከተፈጥሯዊ አወቃቀር ጋርም የተያያዘ እንደሆነ ይናገራሉ።

በወንዶች እና በሴቶች መካከል ያለው ልዩነት የሚቀየር እንዳልሆነ ያክላሉ።

በሴቶች እና ወንዶች መካከል ያለው አንድ ልዩነት የሆርሞን ነው።

በስፔን፣ ቫሌንሺያ ዩኒቨርስቲ የዕድሜ መግፋት ላይ ጥናት የሚሠሩት የሥነ ልቦና ባለሙያ ፕሮፌሰር ኮንሱዌሎ ቦራስ “ኤስትሮጂን ሴቶችን የመጠበቅ ሚና አለው” ይላሉ።

ይህ ሆርሞን የኮሌስትሮል መጠንን የመቆጣጠር፣ የሰውነትን በሽታ የመከላከል አቅም የማስተካከል፣ ከሽንት ትቦ ጋር የተያያዙ ኢንፌክሽኖችን የማስቆም እንዲሁም የአንጎል እና አጥንት ጤናን የመጠበቅ ሚና አለው።

ኤስትሮጂን፤ የሰውነት ሕዋሳት የሚደርስባቸውን ጉዳት የሚከላከሉ (antioxidant) ንጥረ ነገሮች በማምረትም ጠቀሜታ ይሰጣል።

ፕሮፌሰር ኮንሱዌሎ “በማረጥ ወቅት ኤስትሮጂን ማጣት የሰውነትን አሠራር የሚጎዳ ነው” በማለት ያስረዳሉ።

የአጥንት መዳከም (osteoporosis) በኤስትሮጂን መጠን መቀነስ ምክንያት ከሚከሰቱ እክሎች አንደኛው ነው።

ሰውነት ውስጥ ያለውን ተፈጥሯዊ የሆርሞን መዋዠቅ ለማስተካከል ተጨማሪ ሆርሞን በመስጠት የሚከናወነው ሕክምና (hormone replacement therapy) እንደ አማራጭ ይወሰዳል።

ማረጥ በሚጀምርበት ወቅት ይህ የሆርሞን ሕክምና ሲሰጥ የሴቶችን የሰውነት እንቅስቃሴ ለማደስ እንደሚረዳ ባለሙያዋ ያስረዳሉ።

በወንዶች ሰውነት ውስጥ ያለው የቴስቴስትሮን ሆርሞን፤ ራስን ለአደጋ ከሚያጋልጡ ባህሪዎች ጋር የሚተሳሰር ነው።

ሆርሞኑ በሰውነት ውስጥ አሉታዊ ጫና እንዳለው ፕሮፌሰር ኮንሱዌሎ ቢያምኑም ትክክለኛ ጉዳቱ ምን እንደሆነ በትክክል እንደማይታወቅ ይናገራሉ።

በአውሮፓውያኑ 2012 የወጣ ጥናት የተሠራው የዘር ፍሬያቸው እንዲመክን የተደረጉ ኮሪያውያን ላይ ነው።

እነዚህ ወንዶች ሰውነታቸው ውስጥ ቴስቴስትሮን ባለመመረቱ ምክንያት ካልመከኑ ወንዶች በበለጠ ከ14 እስከ 19 ዓመት ኖረዋል።

የጥናቱ ውጤት ውስንነት ቢኖረውም እንሰሳት ላይ የተሠሩ ሌሎች ምርምሮች ተመሳሳይ ግኝት አላቸው።

እነዚህ ግኝቶች ወንዶች ሲመክኑ ዕድሜያቸው እንደሚረዝም ያሳያሉ።

ለረዥም ዓመት የመኖር ምሥጢር የሚፈታው በሆርሞን ብቻ አይደለም። ከግምት ከሚገቡት መካከል ዝግመተ ለውጥ ይጠቀሳል።

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

#ሴቶችወንዶችጤና
#BBChealthage
#ጌጡተመስገንሚዲያናኮሚኒኬሽን
#Getutemesgenmediacommunication


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2