ስጦታ የሚለዋወጡት እንስሳቶች

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ስጦታ የሚለዋወጡት የሰው ልጆች ብቻ አይደሉም።

በእንሰሳት ዓለምም የተለመደ ነው።

ስኮርፒዮንፍላይ የተባለችው በራሪ ነፍሳት ከፍቅረኛዋ የሚሰጣት ስጦታ ምራቅ ነው። ይህም ለስሪያ የሚጋብዝበት መንገድ ነው።

ሌሎች እንደ ቀንድ አውጣና የአፈር ትል ባሉ ነፍሳትና ትላትሎች ዘንድም የተለመደ ነው።

በአብዛኛው ከስሪያ ጋር የተያያዘ የስጦታ ልውውጥ ያከናውናሉ።

በአእዋፍት ዘንድም ይስተዋላል።

ግሬት ግሬይ ሽሪክስ የተባሉት የወፍ ዝርያዎች ወንዶች ሴቶችን ለማማለል እሾሃማ የዛፍ ቅርጫፍ በስጦታ ያቀርባሉ።

በሳይንሳዊ ስሙ አራክኒድ የሚባለው የሸረሪት ዓይትም ስጦታ በመስጠት ይታወቃል።

ነርሰሪ ዌብ ስፓይደር የሚባለው ሸረሪት ለምግብነት የሚውሉ ነፍሳት የበለጠ ማራኪ እንዲሆኑ ኬሚካል አርከፍክፈው ለሴቷ ሸረሪት በስጦታ ያቀርባሉ።

አንዳንድ ሸረሪቶች ጥራቱ የወረደ ወይም በከፊል የተበላ ምግብ በስጦታ ሊያቀርቡ ይችላሉ።

ሴቷ ሸረሪት ስጦታውን ለማየት ጥቅልሉን እስከምትፈታ ድረስ ወንዱ ሸረሪት ስሪያውን አከናውኖ ሮጦ ይጠፋል።

አንድ ጥናት እንደሚያሳየው፣ ወደ 70 በመቶ የወንድ ሸረሪት ስጦታዎች ሐሰተኛ ናቸው።

በዩኒቨርስቲ ኦፍ ቶሮንቶ፣ ካናዳ የእንሰሳት ባህሪ አጥኚ ደሪል ግዌን “የሚያጭበረብሩ ወንዶች ማግኘት የተለመደ ነው።

ያረጀ ነፍሳት ጠቅልለው ስጦታ ለመስጠት ይሞክራሉ” ሲል ያስረዳል።

“ዳንስ ፍላይስ የተባለው ነፍሳት የባሕር ነፍሳት አድኖ ይይዛል።

ሴቶቹ ያደነውን ለመውሰድ ይፎካከራሉ። ምክንያቱም ራሳቸውን መመገብ አይችሉም።

እንቁላል ለማምረት ደግሞ መመገብ አለባቸው” ይላል።

ስጦታ የሚያጭበረብሩ ወንዶች በድጋሚ ከሴት ነፍሳት ጋር ስሪያ መፈጸም አይችሉም።

ሴቷ ስጦታው ሐሰተኛ እንደሆነ ካወቀች በኋላ ከወንዱ ጋር ግንኙነት እንዲኖራት አትፈልግም።

የወንድ የዘር ፍፌው ከእንቁላሏ ጋር የመዋሀድ ዕድሉም ጠባብ ይሆናል።

አንዳንድ ነፍሳት ስጦታ የሚያቀርቡት ራሳቸውን ነው።

ሳገርቡሽ ክሪኬት ክንፉን ሴቷ እንድትበሳውና ደሙን እንድትመጠው ይፈቅዳል።

አንድ ጥናት እንደሚያሳየው፣ አንድ ወንድ ነፍሳት ይህንን ካደረገ በኋላ ከሌላ ሴት ነፍሳት ጋር ግንኙነት የመፍጠር ዕድሉ ይጠባል።

ሌላ የፍቅር ግንኙነት ለመፍጠር ዐቅም ያጥራቸዋል።

እንሰሳት በብዛት ስጦታ የሚሰጡት ለስሪያ ቢሆንም፣ አንዳንዴም ስጦታ በመስጠት ደስታን ለመፍጠር ይሞክራሉ።

ምግብ በስጦታ ሲሰጡ በውስጡ ያለው ንጥረ ነገር ለሴቶች ጠቃሚ ይሆናል።

የእንሰሳት ባህሪ አጥኚ የሆነችው ኒኮላ ክሌይተን “ነፍሳት ስጦታ ሲሰጡ ለስሪያ ነው።

እንደ ጄይ ያሉ አእዋፍ ግን ስጦታ ሲሰጡ ለጉቦ ሳይሆን ለሕይወት አጋርነት መምረጥን ለማሳየት ነው” ትላለች።

እነዚን አእዋፍ በማሰላሰል የላቀ ደረጃ ላይ ያሉና ዕድሜ ልካቸውን ከፍቅር አጋራቸው ጋር የሚኖሩ ናቸው።

እንደ ቁራ ያሉ ወፎች እንደ ሰው ልጆች ስጦታ መስጠት ደስ ስለሚላቸው ነው የሚሰጡት።

#የእንስሳትአለምስጦታ
#ስጦታየሚሰጣጡትእንስሳት
#ጌጡተመስገንሚዲያኮሚኒኬሽን
#Getutemesgenmediacommunication


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: