ኢትዮጵያ ያለባትን የ1 ቢሊዮን ዶላር የውጭ ዕዳ ለመክፈል ከአበዳሪዎቿ ጋር ስምምነት ላይ ደረሰች!ኢትዮጵያ ከዓለም አቀፍ የግል…

- Advertisement -
Sidebar AD
ኢትዮጵያ ያለባትን የ1 ቢሊዮን ዶላር የውጭ ዕዳ ለመክፈል ከአበዳሪዎቿ ጋር ስምምነት ላይ ደረሰች!
ኢትዮጵያ ከዓለም አቀፍ የግል አበዳሪዎች ተበድራው የነበረውን 1 ቢሊዮን ዶላር (ዩሮቦንድ) በወቅቱ መክፈል አቅቷት የነበረ ቢሆንም አሁን ግን ዕዳውን የምታቀልበት የመጀመሪያ ደረጃ ስምምነት ላይ መድረሷን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ።
ኢትዮጵያ ከነበረባት 1 ቢሊዮን ዶላር ላይ የ12% ቅናሽ የተደረገላት ሲሆን በዚህ መሰረት የምትከፍለው ዕዳ ወደ 880 ሚሊዮን ዶላር ዝቅ ብሏል።
ይህንን 880 ሚሊዮን ዶላር እስከ 2029 ድረስ በ6.15% ወለድ በየደረጃው እንድትከፍል ጊዜ የተሰጣት ሲሆን ባለፉት ሁለት ዓመታት ሳትከፍል ያሳለፈችውን 99.4 ሚሊዮን ዶላር የወለድ ዕዳ ትከፍላለች።
ስምምነቱ ወደፊት ኢትዮጵያ ብድር ባስፈለጋት ጊዜ እስከ 1 ቢሊዮን ዶላር ድረስ በድጋሚ የመበደር መብት ወይም ዕድልን ያካተተ መሆኑ ተገልጿል።
ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) እና ዋናዎቹ አበዳሪ ሀገራት (ቻይና እና ፈረንሳይ) ስምምነቱን የደገፉ ሲሆን ይህም የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ገፅታ የሚያሻሽልና ተጨማሪ የውጭ ብድርና 1እርዳታ በቀላሉ እንድታገኝ በር የሚከፍት በመሆኑ .በገበያው ላይ ትልቅ ተስፋን ጥሏል።
በየአብሥራ ተፈራ
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: