የጓደኛውን ሞባይል በመጠቀም ገንዘብ ወደ ራሱ አካውንት ያስተላለፈው ግለሰብ ክስ ተመሰረተበት

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia ||አብርሃም ፈቃዱ የተባለ ተጠርጣሪ በእምነት ያዝልኝ ተብሎ በተሰጠው ስልክ ብር ወደ ራሱ አካውንት በማስተላለፍ የተጠረጠረው ሰኔ 4 ቀን 2018 ዓ/ም ከቀኑ 11:30 በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ሾላ አካባቢ ነው።

‎የግል ተበዳይ ከጓደኛው ጋር ከነበሩበት ምግብ ቤት ካርድ ልግዛ ብሎ ስልኩን ሰጥቶ በወጣበት አጋጣሚ ተጠርጣሪው የግል ተበዳይን የሞባይል ባንኪንግ ሚስጥር ቁጥር በስራ አጋጣሚ ያውቀው ስለነበር 48ሺህ ብር ወደ ራሱ አካውንት ማስተላለፉን በየካ ክ/ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ የአድዋ አካባቢ ፖሊስ መምሪያ ገልጿል።

‎የግል ተበዳይ ጉዳዩን እንዳወቀ ለፖሊስ ያመለከተ ሲሆን ፖሊስም ምርመራውን በመጀመር ወደ ተጠርጣሪው የተላከውን ገንዘብ በማስወጣትና በኤግዚቢትነት በመያዝ መዝገቡ ተደራጅቶ ለአቃቤ ህግ መላኩን ፖሊስ መምሪያው ጠቁሟል።

የተጠናቀረውን የወንጀል መዝገብ የተመለከተው አቃቤ ህግም በተጠርጣሪ አብርሃም ፍቃዱ ላይ ክስ መመስረቱንም ማወቅ ተችሏል።

‎የባንክ የይለፍ ቁጥሮችን ጨምሮ የግል ሚስጥሮችን በአግባቡ መጠበቅ ከመሰል የወንጀል ድርጊት ራስን ማዳን ስለሚያስችል ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባም የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ መልዕክቱን አስተላልፏል።

አዲስ አበባ ፖሊስ


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: