#Ethiopia | የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የአዲስ ኤሌክትሪክ ቆጣሪ ማስገጠሚያ ክፍያን በአንድ ጊዜ መክፈል ለማይችሉ አዲስ ተገልጋዮች የሚሆን የረጅም ጊዜ የክፍያ አማራጭ ነው መዘርጋቱን አስታውቋል።
ይህ አዲስ አሰራር ደንበኞች የቆጣሪ ክፍያውን በሂደት እንዲከፍሉ ዕድል የሚሰጥ መሆኑ ተገልጿል።
ተገልጋዮች የዚህ የጊዜ ገደብ ክፍያ ሥርዓት ተጠቃሚ ለመሆን በመጀመሪያ ማመልከቻ ማቅረብ የሚጠበቅባቸው ሲሆን፥ የማስገመቻ ሙሉ ክፍያውንና ከጠቅላላው የማስቀጠያ ክፍያ ላይ 10 በመቶ የሚሆነውን ቅድመ ክፍያ መፈጸም ይኖርባቸዋል።
ቀሪውን ክፍያ በየወሩ ከሚመጣው የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሒሳብ ጋር አብሮ ለመክፈል የሚያስችል የውል ስምምነት ይፈረማል ተብሏል።
ይህ የክፍያ አማራጭ በአንድ ጊዜ መክፈል የማይቻል መሆኑን የሚያረጋግጥ ምንም ዓይነት ማስረጃ ማቅረብ የማይጠይቅ ሲሆን፥ ለአሁኑ የተፈቀደው ለነጠላ ፌዝ ቆጣሪዎች ብቻ መሆኑ ተጠቅሷል።
በተጨማሪም የተሰጠውን ክፍያ በ6 ወራት ውስጥ ለሚያጠናቅቁ ደንበኞች ከወለድ ነፃ የተደረገ ሲሆን፥ ክፍያውን እስከ 2 ዓመት በሚደርስ የረጅም ጊዜ የጊዜ ሰሌዳ ከፋፍሎ መክፈል እንደሚቻልም ተቋሙ ያደረሰን መረጃ አመላክቷል ያለው አራዳ ኤፍ ኤም ነው።
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
Source: GetuTemesgen









No comments yet.