በሸዋሮቢት ከተማ በደረሰ ከባድ የእሳት አደጋ በመኖሪያ ቤቶችና ንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ!

- Advertisement -
Sidebar AD

#FastMereja I ከሌሊቱ 9፡00 ገደማ፣ በሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር 02 ቀበሌ መግቢያ መንገድ አካባቢ ባጋጠመ ድንገተኛ የእሳት አደጋ በመኖሪያ ቤቶች እና በንብረት ላይ ከፍተኛ ውድመት ደርሷል።

ምንም እንኳን የእሳት አደጋው በንብረት ላይ የከፋ ጉዳት ቢያስከትልም፤ በሰው ህይወትና አካል ላይ ያደረሰው ምንም አይነት ጉዳት አለመኖሩ ተረጋግጧል።

ለጊዜው የዚህ አሳዛኝ የእሳት አደጋ መነሻ መንስኤ ያልታወቀ ሲሆን፤ የከተማው ፖሊስ በአደጋው ዙሪያ ጥብቅ ማጣራት እያካሄደ ይገኛል። ፖሊስ የምርመራውን ውጤት እንዳጠናቀቀ ትክክለኛውን መረጃ ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርግ አስታውቋል።






Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: