የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን ያከናወናቸውን አዳዲስ የጥራት መቆጣጠሪያና የላብራቶሪ ሥራዎች አስተዋወቀ!

- Advertisement -
Sidebar AD

#Fastmereja:-የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን (EFDA) ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡና በሀገር ውስጥ የሚመረቱ የሕክምና ግብዓቶችን ጥራት በላቀ ደረጃ ለመቆጣጠር የሚያስችሉ የላብራቶሪ ምርመራ ሥራዎቹን አስተዋወቀ።

ጥራቱን ያልጠበቀ እና ሀሰተኛ መድኃኒት ወደ ሕብረተሰቡ እንዳይደርስ የሚያደርገውን የቁጥጥር ሥርዓት ይበልጥ ግልጽ ለማድረግ አጠቃላይ ዕድሳት የተደረገለትና ዓለም አቀፍ ዕውቅና ያገኘው የመድኃኒት ጥራት መቆጣጠሪያ ላብራቶሪ በይፋ ሥራ መጀመሩ ተገልጿል።

የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሄራን ገርባ እንደገለጹት፣ ተቋሙ ባከናወናቸው ሰፊ ሥራዎች ዉጤታማ መሆናቸዉን ገልፀዉ የቁጥጥር ሥርዓቷን የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) ML Maturity Level 3 (ML3) ደረጃ ላይ ማድረስ ተችሏል ሲሉ ተናግረዋል።

ይህ የ-ML3 ደረጃ ተቋሙ የተረጋጋና በሚገባ የሚሠራ የቁጥጥር ሥርዓት እንዳለው ማረጋገጫ ሲሆን፣ በመላው ዓለም 70 የሚጠጉ፣ በአፍሪካ ደግሞ ኢትዮጵያን ጨምሮ 9 አገራት ብቻ ናቸው ይህንን ማሟላት የቻሉት። ይህም አገሪቱ በዘርፉ የአፍሪካ የልህቀት ማዕከል ለመሆን ለጀመረችው ጉዞ ትልቅ እምርታ መሆኑ ተገልጿል።

ይህ የ-WHO Maturity Level 3 (ML3) የብቃት ደረጃ ተቋሙ አስተማማኝ፣ በሚገባ የተደራጀና ውጤታማ የቁጥጥር ስርአት (Stable and well-functioning regulatory system) እንዳለው የሚያረጋግጥ መሆኑ ነዉ የተገለፀዉ።

ይህ ጠንካራ አሠራር የሕዝብን ጤና ከመጠበቅ ባለፈ የአገር ውስጥ ምርትን በማበረታታት ለውጭ ንግድና ለኢንቨስትመንት በር የሚከፍት ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ እንዳለዉ ተነግሯል።

እንዲሁም የተቀነባበሩ ምግቦች፣ መድኃኒቶች፣ የሕክምና መሣሪያዎች፣ የውበት መጠበቂያዎች እና የትንባሆ ምርቶች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር ማድረግ የባለሥልጣኑ ቀዳሚ ኃላፊነት መሆኑ ተገልፆ በአሁኑ ወቅት ምርቶች ወደ ገበያ ከመግባታቸው በፊት ጥብቅ ፍተሻ እንዲሁም ክትትል እየተከናወነ እንደሚገኝ ተገልጿል።

እንዲሁም ህብረተሰቡ”የእኔ ጤና፣ በእኔ እጅ” የሚለውን መርህ በመከተል ራሱን ጥራታቸውን ካልጠበቁና አስመስለው ከተሠሩ (Falsified) የሕክምና ምርቶች እንዲጠብቅ አሳስቧል።

#ጤና






Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: