#Ethiopia | በኢትዮጵያ ወጣት ፈጣሪዎች እየተሰራ ያለው “እሁድ ጠዋት” (Sunday Morning) የተሰኘ የአኒሜሽን ተከታታይ ፕሮጀክት በፈረንሳይ በተካሄደው የዓለም ትልቁ የአኒሜሽን ፌስቲቫል አኒሲ (Annecy) እና MIFA Pitches ላይ ሁለት ትልልቅ ሽልማቶችን በማሸነፍ ለኢትዮጵያ የአኒሜሽን ኢንዱስትሪ ታሪካዊ ምዕራፍ ከፍቷል።
ፕሮጀክቱ በበሃገር ልጅ ስቱዲዮ የተዘጋጀ ሲሆን፣ ከ950 በላይ ከቀረቡ ፕሮጀክቶች መካከል 48 ብቻ ለመጨረሻው ዙር ተመርጠው በቀረቡበት ውድድር ውስጥ ሁለት ሽልማቶችን ያሸነፈ ብቸኛ ፕሮጀክት ሆኗል።
በዚህ ውድድር ፕሮጀክቱ ከዋልት ዲዝኒ ካምፓኒ (The Walt Disney Company) እና ከፈረንሳይ የአኒሜሽን ደራሲያን ድርጅት (AGrAF) የተሰጡ ሁለት የMIFA Pitch ሽልማቶችን አግኝቷል።
ይህ ድል በአኒሲ ፌስቲቫል ታሪክ በኢትዮጵያዊያን የተዘጋጀ ፕሮጀክት በዚህ ደረጃ እውቅና ያገኘበት የመጀመሪያ አጋጣሚ ሲሆን፣ ለአገሪቱ የፈጠራ ኢንዱስትሪ ትልቅ እርምጃ እንደሆነ ተገልጿል።
በተጨማሪም “እሁድ ጠዋት” በመጪው መስከረም በደቡብ አፍሪካ በሚካሄደው የDurban FilmMart (DFM) ዓለም አቀፍ የፊልም ፋይናንስ መድረክ ላይ እንዲቀርብ ተመርጧል፤ ይህም ኢትዮጵያ በዚህ መድረክ በአኒሜሽን ዘርፍ ስትወከል የመጀመሪያዋ እንደሚያደርጋት ተጠቁሟል።
ይህ ስኬት የኢትዮጵያ የአኒሜሽን ኢንዱስትሪ በዓለም አቀፍ መድረክ እውቅና እያገኘ መምጣቱን የሚያሳይ ሲሆን፣ ለወደፊቱም ለአገሪቱ ፈጠራ ዘርፍ አዳዲስ እድሎችን እንደሚፈጥር ይጠበቃል።



Source: GetuTemesgen









No comments yet.