#Ethiopia | የዩጋንዳ የጦር አዛዥና የፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ልጅ የሆኑት ጄኔራል ሙሆዚ ካይኔሩጋባ ባስተላለፉት ቀጭን ትእዛዝ በምሥራቅ አፍሪካ ከፍተኛ ተፅዕኖ ያላቸው የሀገሪቱ ቀዳሚ ገለልተኛ ሚዲያዎች ሙሉ በሙሉ መዘጋታቸውንና በወታደራዊ ከበባ ስር መውደቃቸውን አስታውቀዋል።
በዚህ ድንገተኛ እርምጃ ታዋቂው ‘ዴይሊ ሞኒተር’ ጋዜጣ፣ ኤንቲቪ እና ስፓርክ ቲቪ የተባሉ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች በአንድ ጀምበር ከስርጭት ውጭ የተደረጉ ሲሆን የታጠቁ ወታደሮችም በዋና ከተማዋ ካምፓላ የሚገኘውን የሚዲያዎቹን ዋና መሥሪያ ቤት ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥረዋቸዋል።
እርምጃውን ተከትሎ ጄኔራል ሙሆዚ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት “በነጻ ፕሬስ አላምንም፤ ሚዲያ በለውጡ ሰዎች ሊመራ ይገባል” በማለት የተናገሩ ሲሆን አባታቸው ማንኛውንም የሚዲያ ተቋም የመዝጋት ሙሉ ሥልጣን እንደሰጧቸውም ጭምር ገልጸዋል።
ላለፉት 40 ዓመታት በሥልጣን ላይ የቆዩት የ81 ዓመቱ ፕሬዝዳንት ሙሴቬኒ ልጃቸውን ለሥልጣን ተተኪ እያጩት እንደሆነ በሚገመትበት በዚህ ወቅት የተወሰደው እርምጃ በሀገሪቱ ያለውን ከፍተኛ የአምባገንነትና የማፈን ሥርዓት የሚያሳይ ነው በሚል ከተቃዋሚዎችና ከሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ብርቱ ትችት እየቀሰቀሰ ይገኛል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
Source: GetuTemesgen









No comments yet.