የ8ኛ ክፍል የሚኒስትሪ ፈተና ውጤት ዛሬ ከሰዓት ይፋ ይሆናልየ2018 የትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና…

- Advertisement -
Sidebar AD
የ8ኛ ክፍል የሚኒስትሪ ፈተና ውጤት ዛሬ ከሰዓት ይፋ ይሆናል
የ2018 የትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤት ዛሬ ሰኔ 22 ቀን ከሰዓት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ካውንስል አባላት በማለፊያ ነጥቡ ላይ ውይይት ካደረጉ በኃላ ይፋ ይደረጋል ሲል ቢሮው ማስታወቁን ብስራት ሬዲዮ ሰምቷል።
የ2018 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና በአጭር ጊዜ ታርሞ ይፋ መደረጉ ተማሪዎች ለቀጣዩ የትምህርት አመት ከወዲሁ በቂ ዝግጅት እንዲያደርጉ ያስችላል። የ2018 የትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ሰኔ 11 እና 12 /2018 ዓ.ም  በከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ 201 የመፈተኛ ጣቢያዎች ለተከታታይ ሁለት ቀናት ለ56,737 ተማሪዎች መሰጠቱ ይታወሳል፡፡
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: