#Ethiopia | የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በ2018 የትምህርት ዘመን የወሰደውን የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤት ዛሬ ከሰዓት በኋላ ይፋ እንደሚያደርግ አስታወቀ።
ይህ ውጤት ይፋ የሚሆነው፣ የቢሮው የአጠቃላይ ካውንስል አባላት ተማሪዎችን ወደ ቀጣዩ ክፍል የሚያሸጋግረውን የማለፊያ ነጥብ አስመልክቶ ውይይት ካደረጉና ውሳኔ ካሳለፉ በኋላ ነው።
ባለፈው ሰኔ 11 እና 12 ቀን 2018 ዓ.ም በተከታታይ ሁለት ቀናት በተሰጠው በዚህ ከተማ አቀፍ ፈተና ላይ፣ በከተማ አስተዳደሩ ስር በሚገኙ 201 የመፈተኛ ጣቢያዎች ውስጥ 85,737 ተማሪዎች መቀመጣቸው ይታወሳል።
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ
Source: GetuTemesgen









No comments yet.