አመልክቱ ወይም ለቃችሁ ውጡ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በአሜሪካ ጊዜያዊ የጥገኝነት ከለላ አግኝተው የሚገኙ የተለያዩ አገራት ዜጎች ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ ለማግኘት ጥያቄ ማቅረብ ወይም አገሪቱን ለቅቀው መውጣት እንዳለባቸው የአሜሪካ የአገር ውስጥ ደኅንነት ኃላፊ ማርክዌይን ሙሊን አሳሰቡ።

ባለሥልጣኑ ይህንን ማሳሰቢያ የሰጡት የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ባለፈው ሳምንት ያሳለፈውን ውሳኔ ተከትሎ ነው።

አገራቸው ውስጥ ባለው ሁኔታ የተነሳ ጊዜያዊ ከላለ አግኝተው አሜሪካ ውስጥ የሚገኙ የሄይቲ እና የሶሪያ ስደተኞችን ሕጋዊ ጥበቃ በማቋረጥ የተወሰደው እርምጃ እንዲጸና ፍርድ ቤቱ ወስኗል።

ጦርነት፣ ሰብአዊ ቀውስ እና ሰብአዊ መብት ጥሰቶች ከሚካሄዱባቸው አገራት ተሰድደው በአሜሪካ ጊዜያዊ ከለላ ወይም ፒቲኤስ በመባል የሚታወቀውን ፈቃድ አግኝተው የሚኖሩ ከ350 ሺህ በላይ የተለያዩ አገራት ዜጎች ይገኛሉ።

በዚህ አሰራር ምክንያት የአሜሪካ ጊዜያዊ የጥበቃ ከለላ ያገኙ እስከ አምስት ሺህ የሚደርሱ ኢትዮጵያውያን አሉ።

ይሁን እንጂ የአሜሪካ የአገር ውስጥ ደኅንነት መስሪያ ቤት ለሦስት የቆየው የኢትዮጵያውያን ከለላ እንዲቋረጥ ባለፈው ታኅሳስ ላይ ውሳኔ አስተላልፏል።

በ60 ቀናት ውስጥ አገሪቱን ለቅቀው እንዲወጡም አዝዞ ነበር።

ይሁን እንጂ ውሳኔው የሚቃወም አቤቱታ የቀረበለት ቦተስን ውስጥ የሚገኝ የፌደራል ፍርድ ቤት እርምጃውን አግዶት ቆይቷል።

ከሄይቲ እና ሶሪያ ስደተኞችን ጋር የተያያዘውን ተመሳሳይ እግድ ሲመለከት የነበረው የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ባለፈው ሳምንት ባሳለፈው ውሳኔ ግን፤ ፍርድ ቤቶች ይህንን የትራምፕ አስተዳደር ውሳኔ ማገድ እንደማይችሉ አረጋግጧል።

ይህ የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ የኢትዮጵያውያኑ እግድን ጨምሮ በተመሳሳይ ጉዳዮች ላይም ተፈጻሚ እንደሚሆን የሕግ ባለሙያ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

#Usaemigrationvisa
#usalawpolice #BBCnews
#ጌጡተመስገንሚዲያኮሚኒኬሽን
#Getutemesgenmediacommunication


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: