የምረቃዋ ዕለት ቤተሰብ ያልመጣላትን ተመራቂ በደስታ እንባ ያራጩት የባህርዳር ልጆች

- Advertisement -
Sidebar AD

🔥

ባህርዳር ዩኒቨርስቲ ከትናንት ወዲያ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያስተማራቸውን ተማሪዎች በይፋ አስመርቋል። ከነዚህ አንዷ ይህቺ የህግ ትምህርት ቤት ምሩቅ ነች።

ምሩቋ የተመራቂዎች ቤተሰቦች ተሰባስበው በሚመጡበት ዕለት ቤተሰቦቿ አልመጡም ። በዚህም በጣም የተከፋችው ተመራቂ በዶርም ስታለቅስ ቆይታ ተጣጥባ ወደ ከተማ ታመራለች። ከአንድ ካፌም ትቀመጣለች።

በካፌ ተቀምጣ ምግብ በልታና ጠጥታ በዚያ ተክዛ ሳለች፣ ድንገት በቤቱ ያለ ሙዚቃ ወደ ሌላ ይቀየራል። “እንኳን ደስ አላችሁ” ሲል በካፌው ምን መጣ አልኩ ትላለች።

በድንገት ዞር ስትልም ታስቦ እንደተዘጋጀ ነገር፣ 4 የባህርዳር ልጆች ‘እንኳን ደስ አለሽ” የሚል ፅሁፍ ያረፈበትን ኬክ ከሻማው ጋር እንድትቆርሰው ጋብዘው በእንባ አራጭተዋታል።

ይህንን ያልጠበቀችው ተማሪ በብዙ እንባ ደስታዋን የገለፀች ሲሆን ‘እስከ ዛሬ ብቻዬን ነበርኩ። የቅርብ ጓደኛ እንኳን የለኝም። የሚከፋኝም አይመስለኝም ነበር። ነገርግን በእለቱ ከፋኝ። አለቀስኩ። ስወጣም ይህ ሆነ” ስትል ደስታዋን ገልጻለች።

የመጨረሻ ቃሏ ግን ‘አውቃለሁ ይህም ያልፋል” ሆኗል።

Via: ዶች ኤችዲ
#ማህበራዊ





Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: