የጥበብ ሰው መገናኛ መድረክ ተካሄደ

- Advertisement -
Sidebar AD

የባህርዳር ዩንቨርስቲ ፣በአርቲስት ወይንሸት አበጀና በአርቲስት አሸናፊ ማህሌት አዘጋጅነት በብሉ ናይል ሪዞርት (አቫቫንቲ) ትናንት ሰኔ 21 ቀን 2018 ዓ.ም ከሰአት በኋላ በተካሄደው የጥበብ ዝግጅት የተለያዩ ኪነጥበባዊ ዝግጅቶች ቀርበዋል።

በዚህ መርሐ-ግብር አንጋፋ የጥበብ ባለሙያዎች እና የዘንድሮ የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የቴአትርና ሲኒማ ጥበባት ዲፓርትመንት ተመራቂዎች በጋራ ተስናስለው ጥበባዊ ስራዎችን አቅርበዋል ።

በመርሐ-ግብሩ ላይ አየለ አናውጤ (ዶክተር) የአ.ብ.ክ.መ ባህል ቱሪዝም ስፖርት ቢሮ ምክትል ሃላፊ፣ አቶ ግ/ማርያም ይርጋ ባህል፣ ኪነጥበብና ታሪክ ጽ/ቤት ምክትል ሀላፊ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።

የስራ ሀላፊዎቹ አያይዘውም የባህርዳር ከተማን የጥበብ እና የጥበበኞች ከተማ ለማድረግ እየተሰሩ ስላሉ ስራዎች ገለጻ አድርገዋል። ከተማዋ ለምታስበው የጥበብ ከተማነት እቅድም የአንጋፋ የጥበብ ባለሙያዎች ሚና ከፍ ያለ መሆኑን ለዚህም ስኬት ዝግጅት እየተደረገ እንዳለ ተናግረዋል።

አንጋፋ የጥበብ ባለሙያዎችም በተለየ ሁኔታ የዘንድሮ ተመራቂዎች ወደ እውነተኛው የጥበብ አለም ሲመጡ ማስተዋል ስላለባቸው ጉዳዮች የህይወት ልምዳቸውን አካፍለዋል። የከተማዋ ወጣት ከያኒያንም የጥበብ ስራዎችን ለታዳሚው አቅርበዋል።

ሌሎች ስለባህርዳር ከተማ እና የጥበብ ቁርኝት እንዲሁም መሰል መርሐ-ግብሮች በተጠናከረ መንገድ ስለማከናወን መልእክቶች በተላለፉበት ዝግጅት ለዚህ ዝግጅት መቃናት ታላቁን ሚና ለተወጣችው አርቲስት ወይንሸት አበጀ ከከተማው ወጣቶች የክብር ስጦታ እና ሜዳሊያ ተበርክቶላታል። አርቲስት አሸናፊ ማህሌት እና አንጋፋው አርቲስት ተስፉ ብርሐኔም የሜዳልያ ሽልማት ተቀብለዋል።

ደማቅና በርካታ ታድሚያንን ያሳተፈው የጥበብ ሰው መገናኛ መድረክ በአቶ ግርማው አሸብር የባህርዳር ዩንቨርሲቲ የውስጥ ግንኙነት ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ባስተላለፉት የማጠቃለያ መልእክት ተቋጭቷል።

የጥበብ ሰው መገናኛ መድረክ የተቃና እንዲሆን የባህርዳር ዩንቨርስቲ ፣ አባይ ኢንቨስትመንት ግሩፕ፣ ዘመን ኮንስትራክሽን፣ ልህቀት ዲዛይን እና ቁጥጥር ኮርፖሬሽን፣ ብሉ ናይል ሪዞርት እና ቶሎ ትራንስፖርት ድጋፍ አድርገዋል።






Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1