በአዲስ አበባ ከተማ ሙሉ በሙሉ በበይነ መረብ የሚሰጠው የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና በተለያዩ ጣቢያዎች እየተሰጠ ይገኛል

- Advertisement -
Sidebar AD

በአዲስ አበባ ከተማ ሙሉ በሙሉ በበይነ መረብ የሚሰጠው የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና በተለያዩ ጣቢያዎች እየተሰጠ ይገኛል

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ክቡር ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ከምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳምሶን መለሰ እና ከጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሲሳይ እንዳለ ጋር በመሆን ፈተናው ከሚሰጥባቸው ጣቢያዎች መካከል አንዱ በሆነው የአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ተገኝተው የፈተናውን አጀማመር በመመልከት ተማሪዎችን አበረታተዋል።

በከተማ አስተዳደሩ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ የሚወስዱ ተማሪዎች ውጤታማ እንዲሆኑ የማጠናከሪያ ትምህርትን ጨምሮ የተለያዩ ስትራቴጂዎች ተዘጋጅተው ተግባራዊ በመደረጋቸው በከተማ አስተዳደሩ ዘንድሮ የተሻለ ውጤት እንደሚጠበቅ አስታውቀዋል።

ኃላፊው አያይዘውም በከተማ አስተዳደሩ ፈተናው ለ58,309 ተማሪዎች በአራት ዙር የሚሰጥ መሆኑን ጠቅሰው ከ2ሺ በላይ የፈተና አስፈጻሚዎች በየፈተና ጣቢያው ተመድበው ሂደቱን በመከታተል ላይ መሆናቸውንም አስረድተዋል።

#አሐዱ






Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: