ቫንስ ከሩቢዮ ጋር በኢራን እና ሊባኖስ ጉዳይ ተከፋፍለዋል ተባለ
ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን ጋር የደረሱበትን የመግባቢያ ሰነድ በተመለከተ በውስጥ እና በውጭ ትችት እየተሰነዘረበት ባለበት ወቅት የአሜሪካዉ ምክትል ፕሬዚዳንት ጄዲ ቫንስ ስምምነቱን በይፋ ለመከላከል በተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን ቀርበዋል።
ቫንስ በስዊዘርላንድ የተካሄዱትን ከኢራን ጋር ድርድሮች መርተው እንደነበር በመግለጽ የመግባቢያ ሰነዱ ጥሩ እመርታ መሆኑንና ለመጨረሻ ስምምነት ጠንካራ መሠረት መጣሉን ተናግረዋል።
በተጨማሪም ቫንስ እስራኤል በስምምነቱ ላይ ያቀረበችውን ተቃውሞ በጥብቅ በመተቸት ዘጠኝ ሚሊየን ሕዝብ ያላት ሀገር ሁሉንም የብሔራዊ ደኅንነት ችግሮቿን በግድያ ብቻ መፍታት አትችልም ብለዋል።
በሌላ በኩል የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ እስራኤልን በይፋ ከመተቸት ተቆጥበው ትኩረታቸውን በኢራን መንግሥት ላይ አድርገዋል።
ስለ ቫንስ አስተያየት በተጠየቁ ጊዜም ቀጥተኛ መልስ ከመስጠት ይልቅ ሄዝቦላህ በሳምንቱ መጀመሪያ በእስራኤል የፍተሻ ጣቢያ ላይ ስለፈጸመው ጥቃት አንስተዋል።
ይሁን እንጂ የኋይት ሀውስ ኃላፊዎች በቫንስና በሩቢዮ መካከል የፖሊሲ ክፍፍል እንዳለ የሚነሱትን ወሬዎች በማስተባበል ሁለቱም በአስፈላጊ የውጭ ጉዳይ ጉዳዮች ላይ በአንድነት እየሠሩ መሆናቸውን ገልጸዋል።
Ethio Fm
Source: Yeneta Tube









No comments yet.