መምህሩና ተመራቂዋ መምህርት ባለቤቱ ከኮሌጅ ምረቃ ወደ ቤት ሲመለሱ በትራፊክ አደጋ አረፉ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልልካፋ ዞን ቢጣ ወረዳ ደጋ-ኬላ የሚኖሩት መምህር አብሪሃም ግዛው እና ባለቤቱ መምህርት ራሄል አክሊሉ በዛሬው ዕለት በደረሰ አሰቃቂ የትራፊክ አደጋ ህይወታቸው ማለፉ ከዶች ኤችዲ ሰምተናል ።

​መምህርት ራሄል አክሊሉ ከትናንት ወዲያ ከቦንጋ ትምህርት ኮሌጅ በስኬት ተመርቃ የነበረ ሲሆን፣ ባለቤቷ መምህር አብሪሃም ግዛው ደስታዋን ለመካፈል በዚያ ተገኝቶ አንድ ላይ በመሆን የምረቃ ሥነ-ስርዓቱን በጋራ አክብረዋል።

ከ2 ቀናት በኋላ ደስታቸውን አጣጥመው ሳይጨርሱ፣ ከምረቃው መልስ ወደ ቤት በመጓዝ ላይ እያሉ በደረሰባቸው ድንገተኛ አደጋ ሁለቱም ህይወታቸውን ማጣታቸው ብዙሃንን አሳዝኗል።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1