🇲🇦
#Ethiopia | በ2026 የዓለም ዋንጫ የ32 ቡድኖች ጥሎ ማለፍ ዙር በሞንቴሬይ የተካሄደው አስደናቂ ጨዋታ ሞሮኮ ከኔዘርላንድ ጋር 1–1 አቻ ከተጠናቀቀ በኋላ በመለያ ምቶች 3–2 በማሸነፍ ወደ 16 ቱ ጥሎ ማለፍ መግባቷን አረጋግጣለች።
ሞሮኮ በመጀመሪያው አጋማሽ የጨዋታውን ብልጫ ቢይዝም፣ የኔዘርላንድ ግብ ጠባቂ ባርት ቨርብሩገን ባሳየው ድንቅ ብቃት በርካታ የግብ ሙከራዎችን አድኖ ቡድኑን በጨዋታው ውስጥ አቆይቷል።
በሌላ በኩል 100ኛ የብሔራዊ ቡድን ጨዋታውን ያደረገው አሽራፍ ሃኪሚ በቀኝ መስመር ያሳየው እንቅስቃሴ ለኔዘርላንድ መከላከያ ትልቅ ፈተና ሆኖ ነበር።
በ72ኛው ደቂቃ ኮዲ ጋክፖ ለኔዘርላንድ የመክፈቻ ጎል አስቆጥሮ ቡድኑን ቀዳሚ ቢያደርግም፣ በተጨማሪ ሰዓት መጀመሪያ ላይ ኢሳ ዲዮፕ በጭንቅላት ያስቆጠረው ጎል ሞሮኮን ወደ ጨዋታው መልሶ 1–1 አድርጓል።
በመለያ ምቶች የኔዘርላንድ ተጫዋቾች ሶስት ወሳኝ ምቶችን ሲያመክኑ፣ የሞሮኮ ግብ ጠባቂ ያሲን ቦኖ ድንቅ ብቃት አሳይቶ ቡድኑን ወደ ድል መርቷል።
በመጨረሻም እስማኤል ሳይባሪ ወሳኟን የመለያ ምት በማስቆጠር ሞሮኮ 3–2 አሸናፊ ሆና ከጨዋታው ወጥታለች።
ይህ ድል ለሞሮኮ ታሪካዊ ስኬት ሲሆን፣ በ16 ቱ ጥሎ ማለፍ ዙር ከካናዳ ጋር ለሩብ ፍጻሜ የሚያበቃ ወሳኝ ጨዋታ ታደርጋለች። በሌላ በኩል ኔዘርላንድ የውድድሩ ጉዞዋን በልብ ሰባሪ ሽንፈት አጠናቃለች።


Source: GetuTemesgen









No comments yet.