የኛ ሰዎች በሩስያ

- Advertisement -
Sidebar AD

📌ከሦስት አህጉራት የተውጣጡ ጋዜጠኞች በሩሲያ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ስልጠና ተከታተሉ

#Ethiopia | ከሰኔ 15-19 ቀን 2018 ዓ.ም በተካሄደው ስልጠና ኢትዮጵያዊያንን ጨምሮ 22 ጋዜጠኞች ተሳትፈዋል።

በስፑትኒክ የሚዲያ አጋር ሮዚያ ስጎዶንያ እና በሩሲያ የሰብዓዊ ድርጅት ኤጀንሲ ሮዞትሩድቼስትቮ አማካኝነት የተዘጋጀው ይህ ስልጠና የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) በሚዲያው ዘርፍ አጠቃቀም ላይ ያተኮረ ተግባር ተኮር እንደነበር ተገልጿል።

ቴክኖሎጂ ለፍትሀዊ የመረጃ ተደራሽነት ያለው አስተዋጽኦና ተያያዥነት ያላቸው ችግሮች በስፋት መነሳታቸው ተመላክቷል።

የሰው ሰራሽ አስተውሎትን (AI) ለፅሁፍ፣ ትርጉም፣ የድምፅ እና ምስል ቅንብር እንዴት መጠቀም እንደሚገባ በሰፊው ያተኮረ እንደነበር የገለፁት ኢትዮጵያውያን ተሳታፊዎች፣ ቴክኖሎጂ የሰው ልጅን ስራን እንዲተካ ሳይሆን የዕለት ተዕለት ተግባራትን እንዲያቀል አጋዥ ስርዓት መሆኑን መረዳት ችለናል ብለዋል።

ስልጠናው አለማቀፍ እንደመሆኑ መጠን የሚዲያ ዘርፍ እያለፈባቸው ያሉ ተግዳሮቶች በስፋት የተነሱት እንደነበርም ገልፀዋል።

እንደ ቲቃህ ዘገባ ኢትዮጵያ እና ሩሲያ ያላቸው የሁለትዮሽ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የመገናኛ ብዙሃንን ጨምሮ ዘርፈ ብዙ ትብብር እያደረጉ መሆናቸውን የሚያመላክት መሆኑን አብራርተዋል።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: