#Ethiopia | የጅማ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ተማሪና የ“ቤጃይ ኢንዱስትሪያል ኤንድ ኢንጂነሪንግ ሶሉሽንስ” መሥራች እና ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ቢጃይ ናይከር ለተማረበት የጅማ ዩኒቨርሲቲ ከ10 ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያለው ዘመናዊ የእንስሳት መኖ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ በነጻ ሊተክል መሆኑ ተሰማ።
ዩኒቨርሲቲው “ስኬታማና ጀግና ልጅ” ሲል የገለጸው ኢንጂነር ቢጃይ በራሱ ድርጅቱ የሚመረተውን ይህንን ዘመናዊ ፋብሪካ ለተቋም በስጦታ ከመስጠቱም ባሻገር በዩኒቨርሲቲው ለሚገኙ ተማሪዎች የሕይወት ክህሎት ሥልጠናዎችንም እየሰጠ ይገኛል።
በዚሁ ተቋም በኤሌክትሪክ ኢንጂነሪንግ የመጀመሪያ ዲግሪውን ካገኘ በኋላ በትምህርቱ በመግፋት የማስተርስ ዲግሪውን የሠራው ኢንጂነር ቢጃይ ከ300 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ቋሚ የሥራ ዕድል የፈጠረ 24 ንዑስ ተቋራጮችን ያሳደገና የ10 ሚሊዮን ብር የኢኮኖሚ ሽልማት ያሸነፈ ስኬታማ የኢንዱስትሪ መሪ ነው።
በአሁኑ ወቅት በቡርኪናፋሶ ዘመናዊ የሳተላይት ማምረቻ ተቋም ለመገንባት ታላቅ ዝግጅት እያደረገ የሚገኘው ኢ/ር ቢጃይ ለዩኒቨርሲቲው ካደረገው ሰፊ ድጋፍ ጎን ለጎን በዓለም ዙሪያ የሚገኙ የጅማ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ተማሪዎች (Alumni) በሙሉ በይፋ ተመዝግበው ከተቋሙ ጋር እንዲገናኙ ጥሪ አቅርቧል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
Source: GetuTemesgen









No comments yet.