።።።።።።።።
አንድ ትንሽ ልጅ የአባቱን አይን እያየ፦
“አባዬ… በአንድ ሰዓት ስንት ብር ታገኛለህ?”
አባቱም በስራ የደከመ ሰውነቱን ለማሳረፍ ወደ ሶፋ ጠጋ እያለ “ለምን ትጠይቀኛለህ?” አለው።
ልጁ በቀስታ፣ “እባክህ ንገረኝ…” አለ።
“500 ብር።”
ልጁ እንደገና ጠየቀ፦
“250 ብር ልታበድረኝ ትችላለህ?”
አባቱ ተናደደ። “መጫወቻ ልትገዛ ከሆነ አኹን ቀጥ ብለህ ወደ ክፍልህ ሂድ!”
ልጁ ዝም ብሎ ገባ።
ከጥቂት ጊዜ በኋላ አባቱ ተረጋጋ። ወደ ክፍሉ ገብቶ 250 ብሩን ሰጠው።
ልጁም ከትራሱ ስር ያለውን ገንዘብ አወጣ። ሁሉንም ቆጠረ።
አባቱም “ምን እያደረክ ነው?” አለው።
ነገር ግን ልጁ ፈገግ ብሎ እንዲህ አለ፦
“አባዬ… አሁን 500 ብር ሞልቶኛል። ነገ ከእኔ ጋር አንድ ሰዓት ታሳልፋለህ?” አለው።
🕰 Quality Time ውድ ስጦታዎችን አይፈልግም። የወላጅን መገኘት ብቻ ይፈልጋል። በዋናነት አጭር የደቂቃዎች ቆይታ አስር ደቂቃ ሊኾን ይችላል ግን ደግሞ ተከታታይነት የሚፈልግ ሲኾን ሃሳብን ከሚበትን ስክሪን መራቅን ይጠይቃል። በልጆች ሁለንተናዊ እድገት ላይ ተአምራዊ ለውጥ የማምጣት አቅም አለው።
ሰዎች ብዙ ጊዜ የሚያስታውሱት የገዛህላቸውን ነገር ሳይሆን፣ ከእነሱ ጋር ያሳለፍከውን ጊዜ ነው።
💡 ስለዚህ ዛሬ ለልጆቻችን በመገኘት አይረሴ ትዝታዎች ይኑሩን መልዕክቴ ነው።
✍️ ብርሃኑ በላቸው አሰፋ
የክቡር ልጆች ደራሲ ( የ2025 ሕንጸት ተሸላሚ መጽሐፍ)
https://t.me/childdevtnetwork

Source: GetuTemesgen









No comments yet.