ዱባይ ለኢትዮጵያውያን ማስጠንቀቂያየዱባይ ፖሊስ በኢትዮጵያውያን ላይ የመጨረሻ ጥብቅ ማስጠንቀቂያ ሰጠ​ በተባበሩት አረብ ኤምሬቶ…

- Advertisement -
Sidebar AD
ዱባይ ለኢትዮጵያውያን ማስጠንቀቂያ‼️
የዱባይ ፖሊስ በኢትዮጵያውያን ላይ የመጨረሻ ጥብቅ ማስጠንቀቂያ ሰጠ‼️
​ በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በዲጂታል መድረኮች በሚያደርጓቸው እንቅስቃሴዎች ላይ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የዱባይ ፖሊስ እና የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽህፈት ቤት ጥብቅ ማስጠንቀቂያ አስተላልፈዋል። ይህ ማስጠንቀቂያ የተሰጠው በትውልድ ኢትዮጵያውያን መካከል በማህበራዊ ሚዲያ ላይ እየተደረጉ ያሉ አንዳንድ ህገ-ወጥ ድርጊቶችን ለመከላከል ነው።
​የዱባይ ፖሊስ እና የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽህፈት ቤት በጋራ ባዘጋጁት መድረክ እንደተገለጸው፣ በአረብ ኤምሬቶች የሳይበር ወንጀል ህግ መሰረት የሚከተሉት ድርጊቶች ከፍተኛ ቅጣት እንደሚያስከትሉ ተገልጿል፦
📌 ​የጥላቻ ንግግር: በማህበረሰቡ መካከል መከፋፈልን፣ ጥላቻን እና ንቀትን የሚያንጸባርቁ የብሄር ፖለቲካ ቅስቀሳዎችን ሶሻል ሚዲያ ላይ መለጠፍ።
📌 ​ስድብ እና ስም ማጥፋት: ግለሰቦችን ወይም ተቋማትን በቪዲዮ፣ በጽሁፍ ወይም በኮሜንት መዝለፍ እና ስም ማጥፋት ህግ የተከለከለ ነው።
📌 ​ያለ ፈቃድ መረጃ ማውጣት: የግለሰቦችን ግላዊነት የሚነኩ ምስሎችን፣ ቪዲዮዎችን ወይም መረጃዎችን ያለ ፈቃድ ማሰራጨት በህግ የሚያስቀጣ ነው።
📌 ​የገንዘብ ማሰባሰብ: ያለ መንግስት ፈቃድ በማህበራዊ ሚዲያ በኩል በስምምነት ገንዘብ ማሰባሰብ በኢምሬትስ ህግ የተከለከለ ነው።
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1