በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልልካፋ ዞን ቢጣ ወረዳ ደጋ-ኬላ የሚኖሩት መምህር አብሪሃም ግዛው እና ባለቤቱ መምህርት ራሄል አክሊሉ በዛሬው ዕለት በደረሰ አሰቃቂ የትራፊክ አደጋ ህይወታቸው ማለፉ ከዶች ኤችዲ ሰምተናል ።
መምህርት ራሄል አክሊሉ ከትናንት ወዲያ ከቦንጋ ትምህርት ኮሌጅ በስኬት ተመርቃ የነበረ ሲሆን፣ ባለቤቷ መምህር አብሪሃም ግዛው ደስታዋን ለመካፈል በዚያ ተገኝቶ አንድ ላይ በመሆን የምረቃ ሥነ-ስርዓቱን በጋራ አክብረዋል።
ከ2 ቀናት በኋላ ደስታቸውን አጣጥመው ሳይጨርሱ፣ ከምረቃው መልስ ወደ ቤት በመጓዝ ላይ እያሉ በደረሰባቸው ድንገተኛ አደጋ ሁለቱም ህይወታቸውን ማጣታቸው ብዙሃንን አሳዝኗል።

Source: Yeneta Tube









No comments yet.