ተጠንቀቁት!

- Advertisement -
Sidebar AD

* ሴት በመምሰል የማጭበርበር ተግባር ፈጽሟል የተባለ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ዋለ

#Ethiopia | በአዲስ አበባ ጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 አስኮ መናኸሪያ አካባቢ፣ ሴት በመምሰል የማጭበርበር ተግባር ፈጽሟል ተብሎ የተጠረጠረ ግለሰብ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።

እንደ ፖሊስ መረጃ፣ ተጠርጣሪው ጀማል አነስ የተባለ ግለሰብ የሴቶች ሂውማን ሄር፣ የጆሮ ጌጣጌጦች እና የሴቶች አልባሳትን በመጠቀም ራሱን ሴት በማስመሰል ሲንቀሳቀስ ነበር። ከተለያዩ ግለሰቦች ጋር ውይይት በሚያደርግበት ወቅት ጥርጣሬ በመፈጠሩ፣ ለፖሊስ በቀረበ ጥቆማ መሠረት ተይዟል።

ፖሊስ በተጠርጣሪው ላይ ባደረገው አካላዊ ፍተሻ፣ ሴት ሳይሆን ወንድ መሆኑን መረጋገጡን ገልጿል። በተጨማሪም ከተንቀሳቃሽ ስልኩ ውስጥ በተለያዩ ጊዜያት የሴቶች አልባሳትና ጌጣጌጦችን ለብሶ የተነሷቸው ፎቶግራፎች መገኘታቸውን አስታውቋል።

የምርመራ መዝገቡ እና የምስክሮች ቃል እንደሚያሳየው፣ ተጠርጣሪው ከዚህ ቀደምም በተመሳሳይ መንገድ ራሱን ሴት በማስመሰል የማጭበርበር ተግባራትን ሲፈጽም እንደነበር ጥርጣሬ መኖሩን ፖሊስ ገልጿል። ይህ ጉዳይ አሁንም በምርመራ ላይ መሆኑ ተጠቁሟል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ በመጨረሻ እንደገለጸው፣ ለማጭበርበር ወይም ለሌሎች ወንጀሎች ሊውሉ የሚችሉ አጠራጣሪ እንቅስቃሴዎችን ሲመለከቱ ለፖሊስ ፈጥነው መረጃ እንዲያቀርቡ ህብረተሰቡን ጠይቋል።





Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1