መምህሩና አዲስ ተመራቂ ባለቤታቸው ከምረቃ መልስ በደረሰ አደጋ ሕይወታቸው አለፈ::
* መምህር አብሪሃም ግዛው እና
* ባለቤቱ መምህርት ራሄል አክሊ
በካፋ ዞን ሺሾ እንዴ ወረዳ በደረሰ አሰቃቂ የትራፊክ አደጋ የአንድ መምህርና ከኮሌጅ የተመረቀች ባለቤታቸው ህይወት ማለፉ ተሰማ።
አደጋው የደረሰው ከቦንጋ ወደ ሺሺንዳ በመጓዝ ላይ በነበረ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ላይ መሆኑ ተገልጿል።
የሺሾ እንዴ ወረዳ እና የካፋ ዞን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት እንዳስታወቁት፣ የሰሌዳ ቁጥሩ 00582 የሆነው የዶልፊን የሕዝብ ማመላለሻ መኪና ሰኔ 23 ቀን 2018 ዓ.ም ከረፋዱ 5 ሰዓት ከ30 ገደማ ሲሆን ዋና ቦላ በተባለ ቀበሌ ላይ መንገድ ስቶ ወደ ገደል ገብቷል።
ተሽከርካሪው በግምት 50 ሜትር ወደሚሆን ገደል በመግባቱ ምክንያት በውስጡ ተሳፍረው ከነበሩት መካከል ሁለት ሰዎች ወዲያውኑ ህይወታቸው አልፏል።
ህይወታቸው ያለፈው እነዚህ ተሳፋሪዎች መምህሩ እና የኮሌጅ ምረቃዋን አጠናቃ በደስታ ወደ ቤት እየተመለሰች የነበረችው ባለቤታቸው መሆናቸው ተረጋግጧል።
በዚሁ አደጋ ምክንያት ሌሎች የተለያዩ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ተሳፋሪዎች በአቅራቢያው በሚገኘው በዲንቢራ ጤና ጣቢያ ገብተው አስፈላጊው የሕክምና እርዳታ እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ከመንግስት ኮሙኒኬሽን የወጣው ይፋዊ መረጃ ያመላክታል።gursha
ነብስ ይማር 💔
@Seledadotio

Related Posts
- Advertisement -

No comments yet.