በጋምቤላ ክልል ህፃናትን መጠጥ ቤት እንዲገቡ ማድረግ 5 ሺህ ብር ያስቀጣል ተባለ ለአቅመ አዳም ያልደረሱና ዕድሜያቸው ከ18 ዓ…

- Advertisement -
Sidebar AD
በጋምቤላ ክልል ህፃናትን መጠጥ ቤት እንዲገቡ ማድረግ 5 ሺህ ብር ያስቀጣል ተባለ
 
ለአቅመ አዳም ያልደረሱና ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ህፃናት ወደ መጠጥ ቤቶች እንዳይገቡ ለመጠጥ ቤት ባለቤቶች ጥብቅ መመሪያ መስጠቱን በጋምቤላ ክልል አኙዋ ብሔረሰብ ዞን የአቦቦ ወረዳ ሴቶችና ህፃናት ማህበራዊ ጉዳይ ፅህፈት ቤት አስታውቋል። የፅህፈት ቤቱ ኃላፊ ወይዘሮ አዊሊ ኡጁሉ ከብስራት ሬዲዮ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደተናገሩት መመሪያውን ተላልፈው በሚገኙ የመጠጥ ቤት ባለቤቶች ላይ የ5 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት ተላልፋል ።
 
በተጨማሪም ወላጆች ህፃናትን ጫትና የአልኮል መጠጦችን ለመግዛት ወደ ተለያዩ የንግድ ቦታዎች እንዳይልኩ ጥብቅ መመሪያ መተላለፉን ኃላፊዋ ጨምረው ለጣቢያችን ገልፀዋል። ህፃናት ለጤናቸው ሲባል የትኛውንም አይነት የአልኮል መጠጥ ሙሉ ለሙሉ ማስወገድ እንዳለባቸው ተነግሯል ።
 
አልኮል የሚጠጣ ሰው ጤና አደጋ ላይ የሚወድቀው ከእያንዳንዱ መጠጥ የመጀመሪያ ጠብታ ጀምሮ መሆኑን መረጃዎች ያሳያሉ ።የአልኮል መጠጥ የጉበት ካንሰርን ጨምሮ ጉበት ላይ የሚደርሱ ጉዳቶች ፣የልብና የደም ሥር ችግሮች ፣የደም ግፊት ፣የልብ ህመም እንዲሁም የካንሰር ተጋላጭነትን እንደሚጨምር ጥናቶች ይጠቁማሉ።
 
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2