በፕሮግራሙ የሚመረጡ ኢትዮጵያውያን አሸናፊዎች ወደ አውሮፓ በመጓዝ፣ በቡና ስኮላርሺፕ የመኪና ጉዞ (Motorhome) በመሳተፍ፣ የኢትዮጵያን ቡና፣ ባህል እና ቡና ስኮላርሺፕን በዓለም ይወክላሉ።
ከውጭ ሀገራት የሚመረጡ አሸናፊዎች ደግሞ ወደ ኢትዮጵያ በመጓዝ የቡና እርሻዎችን፣ ባህላዊ የቡና ሥነ-ሥርዓትን፣ የኢትዮጵያን ባህል፣ ታሪክ እና ቱሪዝም በቅርብ ይጎበኛሉ።
ቡና ስኮላርሺፕ ቅዳሜ ሰኔ 20 ቀን 2018 ዓ.ም. (27 June 2026) ባዘጋጀው ልዩ የማህበረሰብ ዝግጅት ላይ “Global Coffee Culture Scholarship” የተሰኘውን አዲስ ዓለም አቀፍ ፕሮግራም በይፋ አስጀመረ።
ቡና ስኮላርሺፕ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለ7 ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ስኮላርሺፕ በመስጠት፣ ከዓለም አቀፍ አጋሮች ጋር በመስራት እና ለወጣቶች ዓለም አቀፍ የትምህርት ዕድሎችን በመፍጠር ጉልህ ውጤት አስመዝግቧል። ይህ እንቅስቃሴ የበርካታ ኢትዮጵያውያን፣ ኤርትራውያን እና የሌሎች ሀገር ዜጎች ድጋፍን ያካተተ ነው።
በፕሮግራሙ ላይ በርካታ ኢትዮዽያውያን የተገኙ ሲሆን በተለያየ መንገድ ተማሪዎችን እንደሚደግፉ ተናግረዋል።
Global Coffee Culture Scholarship ትምህርትን፣ የኢትዮጵያን የቡና ባህል፣ ቱሪዝምን እና ዓለም አቀፍ የባህል ልውውጥን የሚያጣምር ፕሮግራም ሲሆን፣ በዓለም ዙሪያ ያሉ የቡና ወዳጆችን በማሳተፍ ለኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ዘላቂ የትምህርት ዕድሎችን ለመፍጠር ተዘጋጅቷል።
የቡና ስኮላርሺፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ቢንያም ፍቃዱ፦
“ቡና ስኮላርሺፕ ኢትዮጵያን በቡና፣ በትምህርት እና በባህል ከዓለም ጋር የሚያገናኝ እንቅስቃሴ ነው። ማንም ወጣት በኢኮኖሚያዊ ችግር ከሕልሙ እንዳይሰናከል እየሠራን ነው።” ብለዋል።
ተቋሙ በየትኛውም የዓለም ክፍል የሚገኙ ኢትዮጵያውያን፣የቡና ወዳጆች፣ ደጋፊዎች እና ዳያስፖራው በGlobal Coffee Culture Scholarship ፕሮግራም እንዲመዘገቡ ጥሪ አስተላልፈው። በየትኛውም የሃገራችን ክልል እና ዓለማችን ክፍል ሚገኙ ኢትዮጵያውያን እንዲመዘገቡ ጥሪ አስተላልፈዋል።


Source: FastMereja









No comments yet.