ቡና ስኮላርሺፕ የ”Global Coffee Culture Scholarship” ፕሮግራምን በስቶክሆልም አስጀመረ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ቡና ስኮላርሺፕ “Global Coffee Culture Scholarship” የተሰኘ አዲስ ዓለም አቀፍ ፕሮግራምን ቅዳሜ ሰኔ 20 ቀን 2018 ዓ.ም. (27 ጁን 2026) በስቶክሆልም በይፋ አስጀምሯል።

ፕሮግራሙ የኢትዮጵያን የቡና ባህል፣ ትምህርትና ዓለም አቀፍ የባህል ልውውጥን በማጣመር ለኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ዘላቂ የትምህርት ዕድሎችን ለመፍጠር ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

በፕሮግራሙ የሚመረጡ ኢትዮጵያውያን ተሳታፊዎች ወደ አውሮፓ በመጓዝ በሞተርሆም (Motorhome) ጉዞ ውስጥ የሚሳተፉ ሲሆን፣ የኢትዮጵያን ቡና፣ ባህልና ቱሪዝም በዓለም አቀፍ መድረክ ያስተዋውቃሉ። ከውጭ አገራት የሚመረጡ ተሳታፊዎች ደግሞ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት የቡና እርሻዎችን፣ ባህላዊ የቡና ሥነ-ሥርዓትን፣ ታሪካዊና ቱሪስት መስህቦችን በቅርብ ይጎበኛሉ።

ቡና ስኮላርሺፕ እስካሁን ለ7 ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ስኮላርሺፕ መስጠቱን ጠቅሶ፣ ከዓለም አቀፍ አጋሮች ጋር በመተባበር ለወጣቶች የትምህርት ዕድሎችን ለማስፋፋት እየሠራ መሆኑን አስታውቋል።

የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ቢንያም ፍቃዱ፣ “ቡና ስኮላርሺፕ ኢትዮጵያን በቡና፣ በትምህርትና በባህል ከዓለም ጋር የሚያገናኝ እንቅስቃሴ ነው። ማንኛውም ወጣት በኢኮኖሚያዊ ችግር ምክንያት ከሕልሙ እንዳይሰናከል እየሠራን ነው” ብለዋል።

ተቋሙ በመጨረሻም በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን፣ የቡና ወዳጆች፣ ደጋፊዎች እና የዳያስፖራ አባላት በ”Global Coffee Culture Scholarship” ፕሮግራም እንዲመዘገቡና እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርቧል።






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: