የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ለ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ አስተዋጽኦ ላበረከቱ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያዎች እውቅና ሰጠ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ዘርፍ፣ በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ሂደት አስተዋጽኦ ላበረከቱ ወረዳዎች፣ ከተማ አስተዳደሮች እና የህዝብ ግንኙነት ባለሙያዎች የእውቅና መርሃ ግብር አካሂዷል።

በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አለሙ ሰውነት፣ የህዝብ ግንኙነት ዘርፉ በምርጫው ወቅት ለህዝቡ ወቅታዊ መረጃ በማድረስ እና የምርጫው ሂደት በስኬት እንዲጠናቀቅ ባሳየው ቁርጠኝነት ከፍተኛ ሚና መጫወቱን ገልጸዋል።

አቶ አለሙ አክለውም፣ በምርጫው የተገኘውን ተሞክሮ በመጠቀም የፓርቲውን እሳቤዎች ለህብረተሰቡ በስፋት ለማድረስ እንዲሁም የህዝብ ግንኙነት ዘርፉ ለሀገር ግንባታና ለአመለካከት ቀረጻ ያለውን ስትራቴጂካዊ ሚና ይበልጥ እንዲያጠናክር ጥሪ አቅርበዋል።

የፓርቲው የፖለቲካና አቅም ግንባታ ኃላፊ አቶ ዘለቀ ከፋለ በበኩላቸው፣ የህዝብ ግንኙነት ዘርፉ በቅድመ ምርጫ፣ በምርጫ ዕለት እና በድህረ ምርጫ ሂደቶች ውጤታማ ስራ መስራቱን ገልጸው፣ ለፓርቲው ስኬት ላበረከቱት አስተዋጽኦ አመስግነዋል። በቀጣይም በብሔራዊ ትርክት፣ በአንድነት፣ በህግ የበላይነትና በልማት ዙሪያ ያሉ መልዕክቶችን በማስፋፋት ዘርፉ የበለጠ እንዲሰራ ጠይቀዋል።

የፓርቲው የወጣቶች ክንፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሚሊዮን የኔው በበኩላቸው፣ 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ፍትሃዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የህዝብ ግንኙነት ዘርፉ የማይተካ ሚና መጫወቱን ገልጸዋል።

በውይይቱ የተሳተፉ አባላትም በምርጫው ሂደት የተገኙ መልካም ተሞክሮዎችንና የታዩ ክፍተቶችን በማንሳት ተወያይተው፣ በቀጣይም የፓርቲውን እሳቤዎች ለማስፋፋት በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ ገልጸዋል።

በመጨረሻም የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት፣ ለሁሉም ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች እንዲሁም ከ1ኛ እስከ 3ኛ ደረጃ ላስመዘገቡ ወረዳዎችና የህዝብ ግንኙነት ባለሙያዎች በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ላበረከቱት አስተዋጽኦ የእውቅና ሽልማት ሰጥቷል።






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1