ኖርዌይ አይቮሪኮስትን 2-1 በማሸነፍ ወደ 16 ቡድኖች አለፈች

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ኖርዌይ በ2026 የፊፋ የዓለም ዋንጫ የ32 ቡድኖች የጥሎ ማለፍ ጨዋታ አይቮሪኮስትን 2-1 በማሸነፍ በታሪኳ አስፈላጊ ድል በማስመዝገብ ወደ 16 ቡድኖች ማለፏን አረጋግጣለች።

ጨዋታው በፍጥነትና በከፍተኛ ፉክክር የታጀበ ሲሆን፣ አንቶኒዮ ኑሳ በ39ኛው ደቂቃ የመጀመሪያውን ጎል አስቆጥሮ ኖርዌይን ቀዳሚ አድርጓታል።

አይቮሪኮስት በ74ኛው ደቂቃ በአማድ ዲያሎ ጎል አቻ ብትሆንም፣ የኖርዌይ ኮከብ ኤርሊንግ ሃላንድ በ86ኛው ደቂቃ ወሳኙን የድል ጎል በማስቆጠር ቡድኑን ወደ ቀጣዩ ዙር አሸጋግሯል።

ሃላንድ በወሳኝ ጨዋታዎች ያለውን ብቃት በድጋሚ ሲያሳይ፣ ኑሳም በጥቃቱ የነበረውን ንቁ እንቅስቃሴ በጎል ለማስጌጥ ችሏል።

በሌላ በኩል አይቮሪኮስት በጨዋታው ሙሉ ጊዜ ጠንካራ ተፎካካሪ ብትሆንም ዕድሎቿን በተገቢው መንገድ መጠቀም ባለመቻሏ ከውድድሩ ተሰናብታለች።

በዚህ ድል ኖርዌይ በ16 ቡድኖች ዙር ከአምስት ጊዜ የዓለም ሻምፒዮኗ ብራዚል ጋር ትገናኛለች። ይህ ግጥሚያ በቀጣዩ ዙር በጉጉት ከሚጠበቁ ፍልሚያዎች አንዱ ሲሆን፣ የሃላንድና የብራዚል ተከላካዮች ፍልሚያ የጨዋታው ትልቁ መነጋገሪያ እንደሚሆን ይጠበቃል።



Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1