ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ከፌደራል መንግስት ጋር የሚደራደር ከሆነ በአዲስ አበባ ከተማ ሳይሆን “በሌላ ሶስተኛ ሀገር” እንደሚሆን ለአሜሪካ ማሳወቁን የፓርቲው ጽህፈት ቤት ኃላፊ ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሔር ተናገሩ።
የአሜሪካ መንግስት “ቪዛ መከልከል ይቅር እና ሌላ ቢያደርግም”፤ “የትግራይ ህዝብ ህልውናን ለማረጋገጥ” ህወሓት “እስከ መጨረሻ እንደሚታገል” ኃላፊዋ ገልጸዋል።
“ሞንጆሪኖ” በሚለው የቅጽል ስማቸው ይበልጡኑ የሚታወቁት ፈትለወርቅ ይህንን የገለጹት፤ ትላንት ማክሰኞ ሰኔ 23፤ 2018 በመቐለ ከተማ በሚገኘው የህወሓት ጽህፈት ቤት ከጋዜጠኞች ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽ ነው።
በትላንቱ ጋዜጣዊ መግለጫ ከተነሱ ጉዳዮች መካከል የፕሪቶሪያ ስምምነት ሁኔታ፣ የጦርነት ስጋት፣ የወጣቶች አፈሳ፣ የአሜሪካ ቪዛ እገዳ እንዲሁም ትግራይን በተመለከተ አሜሪካ እና የአውሮፓ ህብረት ያወጧቸው መግለጫዎች ይገኙበታል።
የፕሪቶሪያ ስምምነት “መፍረሱን” በተደጋጋሚ በሚያወጣቸው መግለጫዎች ያሳወቀው ህወሓት፤ ለዚህም ዋነኛው ተጠያቂ የፌደራል መንግስት መሆኑን ሲገልጽ ቆይቷል።
የህወሓት ጽህፈት ቤት ኃላፊ በትላንቱ መግለጫቸው፤ የፕሪቶሪያ ስምምነትን “የፌደራል መንግስት እንደ መሳርያ ነው የተጠቀመበት” ሲሉ ተመሳሳይ አቋም አንጸባርቀዋል።
“የፕሪቶሪያ ውል እንዲፈጸም ህወሓት ጥረት አድርጓል። ውሉን የሚጥሱ በርካታ ነገሮች ቢሰሩም፤ ‘የፕሪቶርያ ስምምነት ፈርሷል’ ሳይል በትእግስት ቆይቷል። በዚህ ጉዳይ ህወሓት እንደ ፓርቲ ትልቅ ትልቅ መስዋእትነት ከፍሏል” ሲሉም ፈትለወርቅ ለፓርቲው ልሳናት እና ለክልሉ ቴሌቪዥን ጣቢያ ጋዜጠኞች ተናግረዋል።
Via Ethiopia Insider
@Seledadotio

- Advertisement -

No comments yet.