በሐይቅ ላይ የተገነባው የሚሽከረከር ሬስቶራንትና ግዙፉ የአርባ ምንጭ ፕሮጀክት በቅርቡ ይመረቃል

- Advertisement -
Sidebar AD

– ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

#Ethiopia | ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቅርቡ በይፋ ስለሚመረቀው ግዙፍና ማራኪ የአርባ ምንጭ የቱሪዝም ፕሮጀክት አስደናቂ ገጽታዎች ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት በተለይም የስብሰባ፣ ኮንፈረንስና ኤግዚቢሽን (MICE) ቱሪዝምን ታሳቢ አድርጎ የተገነባ መሆኑን ገልጸው፣ በውስጡም በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ማስተናገድ የሚችል እጅግ ግዙፍ አዳራሽ ማካተቱን አስታውቀዋል።

የፕሮጀክቱ አስገራሚ ገጽታ በሐይቁ ውኃ ውስጥ ገብቶ ወደ ላይ በመውጣት የሚሽከረከር ዘመናዊ ሬስቶራንት በመሆኑ ነው ብለዋል።

ይህ የሚሽከረከር ሬስቶራንት በአዲስ አበባ ከሚገኘው የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ዋና መሥሪያ ቤት ሕንፃ ውጭ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሠራ ልዩ የሥነ-ሕንፃ ጥበብ ስለመሆኑም አንስተዋል።

ፕሮጀክቱ ከአርባ ምንጭ ኤርፖርት ከአምስት እስከ ስድስት ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ብቻ የሚገኝና እጅግ ማራኪ በሆነ የመሬት ገጽታ አሠራር ያሸበረቀ በመሆኑ፣ ለማንኛውም ኮንፈረንስና እረፍት ተመራጭ መዳረሻ ያደርገዋል ነው ያሉት።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳብራሩት፣ ጎብኚዎች ወደ አካባቢው ሲያቀኑ በጨንቻ የፖም (አፕል) ምርትን፣ የጫሞን አሳ፣ እንዲሁም ሁለቱን ታላላቅ ሐይቆች ማለትም አባያ እና ጫሞን የሚያገናኘውን ማራኪውን የ”እግዜር ድልድይ” መመልከት ይችላሉ።

ፕሮጀክቱ የተሰራበት አካባቢ ከዚህ በተጨማሪም በነጭ ሳር ብሔራዊ ፓርክ የሚገኙትን የሰዋይኔስ ቆርኬ፣ የሜዳ አህዮች፣ ልዩ ልዩ የአዕዋፋት ዝርያዎች እንዲሁም በማዜ ብሔራዊ ፓርክ የቢልቦ ፍልውኃን፣ የጎሽ መንጋን እና ብርቅዬውን ባለጥቁር ጋማ አንበሳ በቅርበት ማየት የሚያስችል አስደናቂ የተፈጥሮ ጸጋ የታደለ አካባቢ መሆኑን ተናግረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቅርቡ በይፋ የሚመረቀው ይህ ታላቅ የአርባ ምንጭ ፕሮጀክት መንግሥት ከዚህ ቀደም ከሠራቸው ሥራዎች የተማረባቸውንና ያሻሻላቸውን ጥበባዊ ልምዶች በሙሉ ያካተተበት መሆኑን ጠቁመው፣ አዲሱ ፕሮጀክት እጅግ በርካታ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ቱሪስቶችን የሚስብ ግንባር ቀደም መዳረሻ እንደሚሆን ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu
#ArbaMinch #VisitEthiopia #PMAbiyAhmed #MICETourism #EthiopianBroadcastingCorporation


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1