#Ethiopia | ጋዜጠኛ ም/ኢንስፔክተር ሳህለገብርኤል ይትባረክ የፌደራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን የሚዲያ ሃላፊ እንዲሁም የአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ዜና አንባቢ በመሆን ሰኔ 19 ቀን 2018 ዓ.ም. በድንገት ህይወቱ እስካለፈበት ቀን ድረስ ለሀገሩ ብሎም ለተቋሙ የወደፊት መልካም ገፅታ እውቀቱን ጉልበቱን ሳይሰስት ሲያገለግል ቆይቷል።
ጋዜጠኛ ም/ኢንስፔክተር ሳህለገብርኤል ይትባረክ በ18 ዓመቱ የፌደራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽንን በመቀላቀል ለ20 አመታት ያህል ፍትህን መሠረት በማድረግ የህግ ታራሚዎችን በማረምና ማነፅ ሥራዎች ላይ ጉልህ አሻራውን ያሳረፈ ለዛም ማሳያ ከማለፉ ከሁለት ቀን በፊት ለተቋሙን ካለበት ደረጃ ለማሻሻል ያለውን የወደፊት ዓላማውን ከማስቀመጡም በተጨማሪም ያለውን ትርፍ ጊዜ በመጠቀም ከ2008 ዓ/ም ጀምሮ በአዲስ ቴሌቭዥን(አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ) ለ10 አመታት ያህል በጋዜጠኝነት ሙያው ለሀገሩ በትጋት አገልግሏል::
ጋዜጠኛ ም/ኢ/ር ሳህለገበርኤል ይትባረክ እስከ ህይወቱ ህልፈት ድረስ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል ሙሉ ጊዜውን ለሁለቱ ተቋማት በተከበረ ሙያው አገልግሏል።
በመሆኑም ለዚህ መራር እና አስደንጋጭ የሣህለገብርኤል ድንገተኛ ሞት በቀጥታ ተጎጅ ለሆኑት 3 ልጆቹ እና ባለቤቱ ከጎናቸው በመሆን ድጋፍ እንዲደረግላቸው እና በማህበረሰቡ ውስጥ የፈጠረውን አሳዛኝ ክስተት ከተጎጅወች ቤተሰብ ጎን በመቆም በዚህ ሁለገብ እንቁ ጋዜጠኛ ምክትል ኢንስፔክተር የተሰማንን ጥልቅ ሀዘንን በቀጥታ የፌደራል ማረሚያ ቤት ሀላፊ ክብር ኮሚሽነር ጄኔራል የኑስ ሙሉ እና የአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ የስራ ባልደረቦች እና ክቡርት ከንቲባ አዳነች አበቤ በሀዘን የተጎዳውን ህዝብ እና ቤተሰቦችን በሚታይ ተግባር አፅናንቶ አርዓያ የሚሆን በጎ ስራ እንዲሰራ እየጠየቅን ይህንን አይከን የሆነ ወጣት ሁሉም ሰው በይቻላል መንፈስ እንዲያስታውሰው እንጠይቃለን ቤተሰቦቹ ለመንግስት ተቋማት፣ ለግብረ ሰናይ ድርጅቶች እና ለበጎ አድራጊ ግለሰቦችን ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
በፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን የአባሎች መኖሪያ ካምፕ የሚኖሩት የጋዜጠኛ ም/ኢንስፔክተር ሳህለገብርኤል ይትባረክ ቤተሰቦች ለከፍተኛ ችግር ከመዳረጋቸው በፊት ለልጆቹ ምቹ የመኖሪያ ቤት እንዲያገኙ ከማድረግ በተጨማሪ ትምህርታቸውን ባሉበት ሁኔታ ለማስቀጠል እንዲሁም በበዓላት ወቅት ከልጆቹ ጎን መሆን እንደሚገባ ለሚመለከታቸው ተቋማትና አካላት መልዕክቱን ያስተላልፋል።
1000081155457
ጎጃም ይበልጣል ከበደ
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ


Source: GetuTemesgen









No comments yet.