ንብረት ገዝተው የስም ዝውውር ያላደረጉ ዜጎች በአስቸኳይ እንዲያጠናቅቁ ታዘዘ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Eghiopia | ከሪል እስቴት አልሚዎችም ሆነ ከግለሰቦች በሰነዶች ማረጋገጫ ንብረት ገዝተው፣ እስካሁን ወደ መሬት ተቋማት በመቅረብ የስም ዝውውር ያላደረጉ እና የይዞታ ባለቤትነት ማረጋገጫ (ካርታ) ያልያዙ ባለንብረቶች ሂደቱን በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲያጠናቅቁ ጥሪ ቀረበ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ አቶ መኮንን ያኢ ከኤ ኤም ኤን ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደገለጹት፤ የስመ-ንብረት ዝውውር በወቅቱ አለመደረጉ ንብረት ገዝተው የባለቤትነት ማረጋገጫ ያልያዙ ዜጎችን ለተለያዩ ከፍተኛ ጉዳቶች እና ለአደጋ እየዳረገ ይገኛል።

የስመ-ንብረት ዝውውር የመጨረሻ ግቡ ገዥው አካል ህጋዊ የይዞታ ባለቤትነት ማረጋገጫን እንዲይዝ ማድረግ ቢሆንም፣ በተለያዩ ምክንያቶች ይህንን ሳያደርጉ የቀሩ በርካታ አካላት መኖራቸውን ቢሮው ጠቁሟል።

በመሆኑም ቀደም ባሉ ጊዜያት የመኖሪያ ቤትም ሆነ ማንኛውንም በመሬት ላይ ያረፈ ንብረት ገዝተው የስም ዝውውር ያላደረጉ ባለንብረቶች፣ መብታቸውን ለማስከበርና ለከፋ አደጋ እንዳይጋለጡ ሲባል መንግስት በአስቸኳይ እና በአጭር ጊዜ ውስጥ ሂደቱን እንዲያጠናቅቁ ጥብቅ ማሳሰቢያ ሰጥቷል።

#Ethiopia #AddisAbaba #RealEstateEthiopia #LandManagement #AMN #propertylawyerthailand


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: