ወደ ሊዮን ከተማ በረራ ተጀምሯል።

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ፈረንሳይ ሊዮን ከተማ በረራ መጀመሩን ይፋ አደረገ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዓለም አቀፍ ደረጃ የመዳረሻ መረቡን የማስፋፋት ስትራቴጂው አካል የሆነውን ወደ ፈረንሳይ ሊዮን ከተማ የሚያደርገውን አዲስ የመንገደኞች የበረራ አገልግሎት በይፋ ማስጀመሩን አበሰረ።

ይህ አዲስ መስመር ለአየር መንገዱ በፈረንሳይ ሶስተኛ፣ በአውሮፓ ሀገራት ደግሞ 23ኛ መዳረሻ ሆኖ የተመዘገበ ሲሆን፤ በአጠቃላይ የዓለም አቀፍ መዳረሻዎቹን ቁጥር ወደ 146 ከፍ አድርጎታል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው፣ የበረራ አገልግሎቱ መጀመር አየር መንገዱ አፍሪካን ከዓለም ጋር የማገናኘት ተልዕኮውን ለማሳካት የተገኘ ተጨማሪ ስኬት መሆኑን ገልጸዋል።

አክለውም በረራው ለዓለም አቀፍ ተጓዦች ሰፊ አማራጭ ከመፍጠሩም በላይ፣ በሀገራቱ መካከል ያለውን ሁለንተናዊ ትስስር በማጠናከር በኩል ከፍተኛ ፋይዳ እንደሚኖረው አስረድተዋል።

አየር መንገዱ የዘመኑን ቴክኖሎጂ የታጠቁ ግዙፍ አውሮፕላኖችን በመጨመር የመዳረሻ መረቡን የማስፋፋት ስራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል።

በኢትዮጵያ የፈረንሳይ አምባሳደር አሌክሲ ላሜክ በበኩላቸው፣ ሊዮን የኢኮኖሚ እና የንግድ ማዕከል እንደመሆኗ መጠን ወደ ከተማዋ የተጀመረው በረራ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር ትልቅ ሚና ይኖረዋል ብለዋል።

አምባሳደሩ አያይዘውም፣ በቢሾፍቱ እየተገነባ በሚገኘው አዲሱ አየር መንገድ የጥናት እና የቴክኒክ ስራዎች ላይ የፈረንሳይ ተቋማት እየተሳተፉ እንደሚገኙ በመግለጽ፣ በአቪየሽን ዘርፍ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የቆየ ትብብር አድንቀዋል።

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
#ፈረንሳይሊዮን
#ጌጡተመስገንሚዲያናኮሚኒኬሽን
#Getutemesgenmediacommunication




Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1