የ70ዎቹ እና 80ዎቹ የሙዚቃ ወርቃማ ዘመን
#Ethiopia | ድምፃዊት ሜላት ቀለመወርቅ የኢትዮጵያ የሙዚቃ ታሪክ ውስጥ የ“ወርቃማ ዘመን” ተብሎ የሚጠራውን የ70ዎቹ እና 80ዎቹ የሙሉ ባንድ የሙዚቃ ቅርስ በአዲስ መልኩ ለማቅረብ አዲስ ፕሮጀክት ላይ መሥራቷን ገልጻለች።
በፕሮጀክቱ ውስጥ በርካታ ታዋቂ ሙዚቀኞች በሙሉ ባንድ መልክ ተሳትፈዋል። ከእነዚህም መካከል አበጋዝ ክብረወርቅ ሽወታ፣ ሄኖክ ተመስገን፣ ያሬድ ተፈራ፣ ግሩም መዝሙር፣ ዘሪሁን በለጠ፣ ሳሚ ጅፋር እና ሄኖክ ድለቃ ይገኛሉ።
ድምፃዊቷ እንደገለፀችው፣ ፕሮጀክቱ ለመዘጋጀት ብዙ ጊዜ እና ጥረት የፈለገ ሲሆን በቀጥታ የተቀዳ ሙሉ ባንድ ስራ መሆኑ የ70ዎቹ እና 80ዎቹ የሙዚቃ ባህልን ለማስታወስ የተሞከረ መሆኑን ገልጻለች።
በኢትዮጵያ የሙዚቃ ታሪክ ውስጥ ታላቅ ቦታ ያላቸው እንደ ፣ ፣ እና ያሉ አርቲስቶች የፈጠሩት የሙሉ ባንድ ባህል ዛሬም በአዲስ ትውልድ ሙዚቀኞች ሊደገም እየተሞከረ ነው።
“” በሚል ስም የተዘጋጀው ስራ ነገ አርብ 8:00 በድምፃዊቷ የዩቱዩብ ቻናል ላይ ለሕዝብ እንደሚለቀቅ ተገልጿል።
ፕሮጀክቱ የቀድሞውን የሙሉ ባንድ የሙዚቃ ክብር ወደ ዘመናዊ አቀራረብ ለማምጣት የተደረገ ጥረት መሆኑ ተጠቅሷል።
ጋዜጠኛ መሉቀን አስን
Source: GetuTemesgen









No comments yet.