#Ethiopia | በስኮትላንድ የማሳጅ መሳሪያን ወይም (Massage Gun) ለአይኑ የተጠቀመው ወጣት ለከባድ እይታ ችግር ተጋልጧል።
ወጣቱ የአይን ድካምን ለማስታገስ “ማሳጅ ገን” ለአራት ወራት ያህል ሲጠቀም መቆየቱን ተናግሯል።
ይህንንም ተከትሎ በአይኑ ውስጥ በርካታ የሬቲና እንባዎች (Retinal tears) እንዲሁም የአይን መጎዳት እንዳስከተለበት ታውቋል።
ወጣቱ ፈጥኖ ወደ ህክምና ቦታ በመሄዱ የሌዘር ህክምና ተደርጎለት የሬቲና ስብራቶቹ እንዲጠገኑ ተደርጓል ተብሏል።
የህክምና ባለሙያዎች እንደገለጹት እነዚህ መሳሪያዎች ለትላልቅ የሰውነት ጡንቻዎች እንጂ ለስሱ ወይም ለፊት እና ለአይን ክፍሎቻችን ፈጽሞ የተዘጋጁ አለመሆናቸውን ተናግረዋል።
በመሆኑም ተመሳሳይ መሳሪያዎችን ሲንጠቀም ከፊት ከአይን እና ከአንገት አካባቢዎች ሙሉ በሙሉ ማራቅ ያስፈልጋል ብለዋል።
እነዚህን የመሰሉ የማሳጅ መሳርያዎች ለጡንቻ ስፖርቶች ላይ ብቻ እንዲጠቀሙ ሲሉ ምክራቸውን አስተላልፈዋል።
በሔኖክ ወ/ገብርኤል
#Ethiopia #GetuTemesgen #GetuNews
#Scotlandhospital
#Eyecareinformation
Source: GetuTemesgen








No comments yet.