አንካራ በሰማይም በምድር ተሰናድታለች

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ተርክዬ 36ኛው የኔቶ የመሪዎች ጉባኤ ለማስተናገድ ከፍተኛ ዝግጅት እያደረገች ትገኛለች።

ተርክዬ በሚቀጥለው ሳምንት ማክሰኞ እና ረቡዕ በአንካራ ለምታስተናግደው 36ኛው የኔቶ የመሪዎች ጉባኤ ከፍተኛ ዝግጅት እያደረገች ትገኛለች።

የሀገሪቱ መከላከያ ተቋም መሪዎችን ለመቀበል ወታደራዊ ዝግጅት እያደረገ እንደሚገኝ አስታውቆ በእለቱ የተርክዬን ስልጣኔ የሚያሳይ ወታደራዊ ትርኢት እንደሚያቀርብ ገልጿል።

ጉባኤው በሰላም እንዲጠናቀቅ የደህንነትና የፀጥታ ስራዎች አስቀድሞ መጨረሱን የገለፀው ተቋሙ ሌሎች የመንግስት ተቋማትም ዝግጅታቸውን በማጠናቀቅ ላይ ይገኛሉ ብሏል።

ከጉባኤው ጎን ለጎን የመከላከያ ኢንዱስትሪ ተቋማት የተርክዬ ኤሮስፔስ ኢንዱስትሪዎች (TUSAŞ) ማዕከልም የዘርፉን ልዕቀት የት እንደደረሰ ያለመ የውውይት መድረክ ያቀርባሉ ተብሏል።

የተርክዬን የመከላከያ አቅም እና ወታደራዊ መሳርያዎች ለዓለም አቀፍ ማህበረሰብ በዝግጅቱ ለሚታደሙ መሪዎች ያስተዋውቃሉ ተብሏል።

በሀገር በቀል ቴክኖሎጂ የተሰሩ የአየር ላይ መድረኮች (aviation platforms) የሙከራ በረራዎችን ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የአጋር ሀገራትን የጋራ ደህንነት እና የመከላከያ ትብብር ለማጠናከር ያለመ ነው።

ተርክዬ በ2004 በኢስታንቡል ካስተናገደች በኋላ ለሁለተኛ ጊዜ ይህንን ዓለም አቀፍ ጉባኤ ለማስተናገድ ሙሉ ዝግጅቷን እያጠናቀቀች እንደምትገኝ አናዱሉ ዘግቧል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

​#Ethiopia #GetuTemesgen #GetuNews
#Turkey #NATOSummits #Ankara #TUSAS


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2