#Ethiopia | የካንሰር ሕክምናዋን አጠናቃ ሙሉ በሙሉ ወደ ማገገም የተመለሰችው የዌልሷ ልዕልት ኬትሪን ካጋጠማት ከባድ የሕይወት ፈተና በድል መውጣቷን በዝምታ ከማሳለፍ ይልቅ ለካንሰር ሕሙማን እንክብካቤ ድጋፍና ግንዛቤ ለመፍጠር ታላቅ ዓላማ ሰንቃ ተነስታለች።
ልዕልቷ የብሪታንያን አድካሚና ከፍተኛ ጉልበት የሚጠይቀውን ሦስት ታላላቅ ተራሮች የመውጣት ውድድር በተሳካ ሁኔታ አጠናቃለች።
በዚህም መሠረት በስኮትላንድ፣ በእንግሊዝና በዌልስ የሚገኙትን ከፍተኛ ተራሮች ማለትም ቤን ኔቪስ፣ ስካፌል ፓይክ እና ስኖውዶንን በ24 ሰዓታት ውስጥ ብቻ በመውጣትና በመውረድ፤ በረጅም ርቀት የእግር ጉዞ፣ በድንቅ ጽናት የታጀበ አስደናቂ አካላዊ ብቃቷን አስመስክራለች።
ይህ ጉዞ ከተራ አካላዊ ፈተናነት ባለፈ ለልዕልት ኬትሪን ጥልቅ ትርጉም ያለው ሲሆን ከካንሰር ምርመራና ሕክምና በኋላ ሕይወትን በአዲስ መልክ ለመቃኘት እንዲሁም በሕክምናው ሂደት ከጎኗ ለነበረው የሆስፒታል ማኅበረሰብ ውለታን ለመመለስ የተጠቀመችበት ትልቅ ዕድል መሆኑን ገልጻለች።
ከባድ ሕመምን ተከትለው የሚመጡትን ስሜታዊ፣ አእምሯዊና ግላዊ ተግዳሮቶች ላይ የሰዎችን ትኩረት ለመሳብ ያለመው ይህ የልዕልቷ አርአያነት ያለው ጥረት በማጠናቀቂያው ከፍታ ላይ በባለቤቷ ልዑል ዊሊያም፣ በልጆቿና በቅርብ የቤተሰብ አባላት ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል።
ይህ ልብ የሚነካ ታሪካዊ ወቅት ፈተናውን በስኬት ማጠናቀቋን ብቻ ሳይሆን በሂደቱ ውስጥ ያሳየችውን ጥንካሬ የማይበገር ጽናትና የምስጋና ልብ በጉልህ ያሳየ ሆኗል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
Source: GetuTemesgen









No comments yet.